የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ የማጠቃለያ የምርጫ ቅስቀሳ መርኀግብር በድምቀት ተካሄደ።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከየካቲት 8 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅቶች ነበሩ። ግንቦት 28 ይደረጋል በተባለው ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳው የሚያበቃው በግንቦት 23 ነበር። ሆኖም ምርጫው ወደ ሰኔ 14 መዛወሩን ተከትሎ የምርጫ ቅስቀሳውም አብሮ መራዘሙ ይታወሳል። የምርጫ ቅስቀሳው ከመጭው አርብ በፊት ተጠናቆ ምንም ቅስቀሳ ወደማይካሄድበት ወደ የጥሞና […]

የትምህርቱ ዘርፍ ችግሮቻችን በብልጽግና ይፈታሉ

ከኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት ከፍተኛ ሀብት ሲመደብለት የቆየው የትምህርት ዘርፍ፤ ከፍተኛ የጥራትና የተደራሽነት ችግር የሚታይበት በመሆኑ ፓርቲያችን ብልጽግና ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ልዩ ትኩረት በመስጠት ችግሩን ለማቃለል ጥረት አድርጓል፡፡ እንደሚታወሰው፤ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ በየአምስት (ስድስት) ዓመታቱ ልዩነት ክለሳ ሊደረግበት የሚገባ ቢሆንም፤ ፖሊሲው ከ20 ዓመታት በላይ ሳይታይ ቆይቷል፡፡ ከብልጽግና በፊት በነበሩ 15 ዓመታት ትኩረት የተሰጠው የትምህርት ማስፋፋት ነበር፡፡ […]

ብልጽግናና መልካም እሴቶች አይነጣጠሉም!!

ኢትዮጵያውያን በዘመናት ውስጥ እርስ በርስ ተሳስረዋል፤ በጠበቀ ማንነት ተጋምደዋል። በዓለም ዘንድ ታላቅ በሚያደርጋቸው እነርሱነታቸው ተሰናስነዋልም። የእነርሱ ጥብቅ መተሳሰር የመጣው በዘመናት ሂደት ነው። ለዚህ የተለያዩ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል። በዘመናት ውስጥ ደማቸውን ቀለም፣ አጥንታቸውን ብዕር አድርገው የጻፉትን መልካም ታሪክ ዋቢ ማድረግ እንደሚቻል ብልጽግና ፓርቲ ያምናል። በብልጽግና አተያይ ኢትዮጵያውያን ከውጭ የመጣን ጠላት ለመከላከል፣ ለማጥቃትና የጋራ ክብራቸው እንዳይገሰስ ለማድረግ […]

“የብልጽግና ጉዞ” – አስታራቂ ትርክት ፍለጋ!!

ባለፉት ሦስት ዓመታት አዲስ ዓይነት የፖለቲካ ትርክት ብቅ ብሏል። የብልጽግና ትርክት። ሀገራችን በአንድነት ጸንታ እንድትቆይ ብቻ ሳይሆን፣ የግለሰቦች ነጻነትና የቡድኖች እኩልነት የወንድማማች እሴትን አቅፈው እንዲተገበሩ የሚሻ ዓይነት ትርክት ነው። ከእኩልነትና ከነጻነት ተቃርኖ የተወለዱት የዘመናት የፖለቲካ ችግሮቻችን በዴሞክራሲና በወንድማማችነት እሴት ባለመደገፋቸው የተባባሱ ናቸው ብሎ ብልጽግና ያምናል። ከዚህ ቀደም የተፈጠሩ ትርክቶች አስታራቂና የኢትዮጵያን ችግሮች በምሉዕ እይታ ያልዳሰሱ […]

የውጭ ምንዛሬ ተመን፣ የወጪ ንግድ ገቢ እና የዋጋ ንረት

የውጭ ምንዛሬ ተመን፣ የወጪ ንግድ ገቢ እና የዋጋ ንረት በአንድ ወቅት የሚኖር የውጭ ምንዛሬ ተመን ምጣኔ ወይም የብር ከአሜሪካን ዶላር አንጻር ያለው ዋጋ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ላይ ቀጥተኛና ጠንካራ የሆነ ተፅዕኖ አለው፡፡ የአንድ አገር የውጭ ምንዛሬ ግኝት በዋነኝነት ከአራት ዋና ዋና ሁነቶች ይመነጫል፡፡ እነዚህም ሀገሪቱ ወደ ውጭ ሀገር ሸቀጦችንና አገልግሎቶችን በመላክ የሚታገኘው […]

የእርሶ ድምፅ ዋጋ አለው

ምርጫ ብሄሮች ፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች በማንኛዉም ሁኔታ ልዩነት ሳደረግባቸዉ በቀጥታ፣በነጻነትና በሚስጥር በመረጡዋቸዉ ተወካዮቻቸዉ አማካይነት ራሳቸዉን በራሳቸዉ ለማስተዳደር እንዲመራቸዉ ፈቃዳቸዉን የሰጡት ብቻ እንዲመራቸዉ ለመምረጥ እድል የሚያገኙበት የዴሞክራሲ ሒደት ነዉ፡፡ የፊታችን ግንቦት ወር ለስድስተኛ ጊዜ የሚካሄደው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ነጻ፣ሰላማዊ፣ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ ይጠናቀቅ ዘንድ ብልጽግና ፓርቲ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ እየሰራ ይገኛል፡፡ ነጻ፣ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ስንል ምርጫ […]

ብልጽግናን ይምረጡ

በሀገራችን የተፈጠረዉን የለውጥ ማዕድ ተቋዳሽ ለመሆን የበቁበት የለዉጡ ትሩፋት መሆኑና የተጀመረዉ ሀገራዊ ለውጥ እየጎመራና እየፈካ ሄዶ ለዓመታት በህዝቡ ዘንድ ሲነሱ የቆዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ ትግሎች እንዲሳኩ ያደረገዉንና ግዙፉን ጨለማ የገፈፈዉና ያሸነፈዉን የጨለማ ንጉስ የሆነዉን የበራውን አምፖል በመመረጥና የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በማሳካት በሀገራችን ለዘመናት በጨለማ የኖረውን ገጠራማውን ክፍል በአምፖል እንዲበራ ብልፅግናን በመምረጥና ይህንን […]

ብልጽግና – የሴራ እና የመጠላለፍ ፖለቲካን በሀሳብ ልዕልና ድል የነሳ ፓርቲ!

የኢትዮጵያ የሦስት ሺህ ዓመት ታሪክና ስልጣኔ ባለቤትነት፣ ያልተቆራረጠ የመንግስት አስተዳደር ስርዓት እንዲሁም የአገረ መንግስት ግንባታ ያላት አገር ናት የምንለው ለዚህ እውነታ በርካታ አብነቶችን ማቅረብ ስለምንችል ነው፡፡ እንደ አክሱም፣ ላሊበላ፣ ፋሲለደስና የጀጎልን ስነህንጻ ጥበቦችን አጣቅሰን፤ የራሷን የቀን አቆጣጠርና ፊደል ቀርጸው ያለፉ ጠቢባንን እማኝ አድርገን፤ ለዲሞክራሲ ስርዓት እውን መሆን እድሜ ጠገቡን የገዳ ስርዓትና ሌሎችንም አያሌ የኢትዮጵያውያን ቱባ […]

ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያን እንገነባለን! እኛ ብልጽግና ነን!

ኢትዮጵያ የብሔር፣ የባህል፣ የሐይማኖት፣ የፖለቲካ አመለካከት ወዘተ ብዝሃነት ያላት፤ በዚህም መነሻ፤ የተለያዩ ጥቅሞችና ፍላጎቶች የሚንጸባረቁባት አገር ናት፡፡ ስለሆነም የምትገነባው ኢትዮጵያ የእምነት፣ የብሔር እና የፖለቲካ አመለካከት ወይም የጥቅም እና የፍላጎት ብዝሃነት የምታንፀባርቅ መሆን ይኖርባታል፡፡ ይህን በአግባቡ የተረዳውና ለጉዳዩም ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ ትግል የጀመረው ፓርቲያችን ብልጽግና ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያን የመገንባትን አስፈላጊነትን በፖለቲካ ፕሮግራሙ ከመግለጽ ባሻገር፤ ባለፉት ሦስት […]

እኛ ብልጽግናዎች ቃላችንን ነን!

ሁሌም ቃላችንን እናከብራለን፤ ለዚህ ቅንጣት ጥርጥር የለንም። በፈተናዎች ብንከበብም፣ በችግር ሸለቆ ውስጥ ብናልፍም፣ ሜዳው ዳገት እንዲሆንብን የሚተጋ ኃይል ቢኖርም ቃላችንን እናከብራለን። እኛ ብልጽግናዎች ቃላችንን ነንና። ቃል እውቀትንና እውነትን መሰረት ሲያደርግ ጥንካሬ ይሰጣል። ተግባራዊ ለማድረግም አቅም ይሆናል። እኛ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት በወንድማማችነት ያስተሳሰሩ የማንነት መገለጫዎች፣ ዓለምን ያስደመሙ ድንቅ እሴቶች፣ ባህልና ወጎች እንዳሉን እናምናለን፤ የእምነታችን ምንጩ እውቀት ነው። […]