የፓርቲያችን ዋነኛ ዓላማ ኅብረ ብሔራዊነቱ የተጠበቀ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መገንባት ነው። ህብረ ብሔራዊ ስንል የብሔር፥ የሃይማኖት ወይም ሌላ ማንነቶችን ያቀፈና ማንንም ያላገለለ ማኅበረሰብ ማለታችን ነው።
የፓርቲያችን ኅብረ ብሔራዊነት በሁሉን አቀፍነት፣ በብዝኃ ልሳንነት እና በአሳታፊነት ሊገለጽ ይገባል ብሎ ፓርቲያችን ያምናል።
ህብረ ብሔራዊ አንድነት ብዝኃነትን እንደጸጋ የሚመለከት ለሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ዕውቅና የሚሰጥና ካላቸው የታሪክ ትሥሥር ተመሳሳይ አሁናዊ ሁኔታና የጋራ ጥቅም እና ተስፋ በመነሳት ጠንካራ ኅብረትና ትብብር ሊኖራቸው ይገባል የሚል ዕሴት ነው።
ህብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ማንነታችን እርስ በርሱ የተጋመደ፣ የተሠናሰለ እና የተዋሐደ መሆኑን አመላካች ነው። ህብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ዕጣ ፈንታችን እጅጉን የተቆራኘ መሆኑን በመገንዘብ ለጋራ ዓላማና ግብ አብረን መቆም፣ አብረን መሥራት፣ መደጋገፍ እና መተጋገዝ እንደሚገባን የሚያስገነዝብ አመለካከት ነው።
ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ታሪካዊና ነባራዊ በደሎች ከማድበስበስ ይልቅ ታርመው እንዲሄዱ ይህም ለቁርሾ ሳይሆን ወዳጅነትን ለማጠናከር እንዲውል የሚያደርግ አካሄድ ነው።
ህብረ ብሔራዊ አንድነት የሚከፋፍሉ እና የሚያጣሉ ትርክቶችን ከማጉላት ይልቅ የሚያቀራርቡና የሚያስተሣሥሩንን እውነታዎች በማጉላት ከትናንት ጠቃሚ ትምህርቶችን በመውሰድ እንዲሁም ዛሬና ነገ ላይ በማተኮር እህታማማችነትና ወንድማማችነት ኅብረትን በብሔሮች መካከል ማጠናከርን ይመርጣል።
በብዝኃነታችን ደምቀን በአንድነታችን በርትተን ወደፊት የምንራመድበት የውበትና የጥንካሬያችን ምንጭ ነው። ኅብረ ብሔራዊ አብሮነት እነዚህ ምሦሶዎች ከተሳኩ በኋላ የሚመጣ ብቻ ሳይሆን ለዓላማዎች ስኬትም ዓይነተኛ ድርሻ የሚወጣ አስቻይ አቅም በመሆኑ ፓርቲያችን “በኅብረት ሆነን እንበለጽጋለን፤ በልጽገንም በኅብረት እንኖራለን” በሚል መርሕ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው።
Leadership

አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ አህመድ
የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ
Prosperity Party Dire Dawa Admin/Branch Office Head

አቶ ሻክር አህመድ አሊ
የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ እና
የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ
Deputy Head Of Branch Office and Head Of Political
and Capacity Building Sector

አቶ ደረጀ ፀጋዬ ተመስገን
የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ
Head, Organization Sector

አቶ ገዛኸኝ ታዲዮስ ጅፋሮ
የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ልዩ ረዳት
Special Assistant to the Head
of the Branch Office

ኢንጂነር ኡመር ዱዓሌ
የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
Head, Public Relations Sector

አቶ ሰይፈዲን አብዱረህማን ሳሊህ
Seyfedin Abdurehman Salih የሀብት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ Head, Resource Management Sector
