ሙስናን በሚመለከት
“ሌብነት ነቀርሳ ነው፤ ሀገርን ይበላል፡፡ ትንሽም ሆነ ትልቅ ሌብነት መጥፋት አለበት፡፡ ለዚህም ነው መንግስት የህግ ማሻሻያዎችን እያደረገ ያለው፡፡ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅም ይህን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት ግለሰቦች በህገ ወጥ መንገድ በርካታ ቢሊዮኖችን ያንቀሳቅሳሉ፤ ይህን መጠየቅ የሚችል ህግ አልነበረንም፡፡ አዋጁ ይህን ችግር በመቅረፍ የህግ ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ነገር ግን አዋጁ ያጠቃናል ያሉ ሌቦች ከወዲሁ የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት ህዝብን ለማደናገር እየሞከሩ ነው፡፡ በመሆኑም ሌብነትን በመታገል ረገድ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተግባር የተጨበጠ ስራ ማከናወን አለበት