መንግስት በሰለጠነ መንገድ ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ ቅድሚያ መስጠቱን እንደ ድክመት የሚቆጥሩ ካሉ፤ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንካራ ነው” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

“መንግስት በሰለጠነ መንገድ ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ ቅድሚያ መስጠቱን እንደ ድክመት የሚቆጥሩ ካሉ፤ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንካራ ነው” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

*******************

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው፤ ባለፉት ጊዜያትም መንግስት ለሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ በሆደ ሰፊነት በርካታ ስራዎች ሰርቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በግጭትና ጦርነት ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣን መያዝ ፈጽሞ አይቻልም ብለዋል፡፡

መንግስት በሰለጠነ መንገድ ችግሮች በውይይትና ድርድር እንዲፈቱ ቅድሚያ መስጠቱን እንደ ድክመት የሚቆጥሩ ካሉ፤ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንካራ መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከግጭት ታሪክ ነጻ ወትታ አታውቅም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስተሩ፤ ይህ የመገዳደል ታሪክ በእኛ ትውልድ ሊቆም ይገባል፤ መንግስት ለሰላም የሚከፈል ማነኛውንም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነው ሲሉም ገልፀዋል፡፡

አያቶቻችን የተዋጉት ቅድም አያቶቻችን ባቆዩላቸው ፀብ ነው፤ አባቶቻችን የተዋጉት አያቶቻቸው ባቆዩላቸው ፅብ ነው፤ እኛም አሁን የምናዋገው የአባቶቻችንን ፀብ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በአንድ የክብሪት ስንጥር እሳት እንደሚለኮሰው ሁሉ ጦርነትንም መለኮስ እና መጀመር ቀላል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በቀላሉ የተነሳውን ጦርነት ማቆም እና የሚያስከትለከውን ጥፋት መቆጣጥር ግን አስቸጋሪ ብለዋል፡፡

ብዙ አስደማሚ ውጠቶችን እያስመዘገበች ሃገር በትንንሽ ጉዳዮች ጉዞዎ እንዲደናቀፍ፤ ስሟ እንዲጎድፍ፣ የጀመረችው የዲሞክራሲ ግንባታ እንዲስተጓጎል የሚሰሩ ሰዎች አሉ ብለዋል፡፡

ይሁንና በግጭትና ጦርነት ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣን መያዝ ፈጽሞ የማይቻል ጉዳይ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በግጭት፣ በጦርነት እና በመፈንቅለ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣን መያዝ ማለት ብሎኑ የተበላሸበት ጥርስ እንደማለት ነዉ ሲሉም አክለዋል።

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *