በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ አመራሮች እየተሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬም ለሶስተኛ ቀን እንደቀጠለ ነው

በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ አመራሮች እየተሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬም ለሶስተኛ ቀን እንደቀጠለ ነው ።ለ5 ተከታታይ ቀናት ” አዲስ ፖለቲካዊ እይታ – አዲስ አገራዊ እምርታ ” በሚል መሪ ሀሳብ በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ አጠቃላይ ለብልፅግና ፖርቲ አመራሮችና ለፌደራል ተቋም አመራሮች መሰጠት የተጀመረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬም ለሶስተኛ ቀን ቀጥሏል።ትላንት የአስር አመቱ የፓርቲና የመንግስት እቅድና፣ የአመራሩ ሚና እና ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ረዳት የመንግስት ተጠሪና የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ የሆኑት አቶ ሻኪር አህመድ እንዲሁም በዛሬው እለትም ኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ለውጤታማ አመራር ሰነድ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አሊይ ቀርበዋል ።በቀረቡ ሰነዶች በየቡድኑ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸው በማዕከል በመጠቅለል አመራሩ በአስሩ አመት እቅድ አፈጻጸምና በሚዲያ ስራዎች የመሪነት ሚና በአግባቡ የሚጠበቅበትን መወጣት እንዳለበት የጋራ መግባባት ተፈጥሮባቸዋል።በቀጣይ ሁለት ቀናት የመስክ ጉብኝትና የመጨረሻው ሰነድ የሚቀርብ ይሆናል።

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *