የትምህርቱ ዘርፍ ችግሮቻችን በብልጽግና ይፈታሉ

ከኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት ከፍተኛ ሀብት ሲመደብለት የቆየው የትምህርት ዘርፍ፤ ከፍተኛ የጥራትና የተደራሽነት ችግር የሚታይበት በመሆኑ ፓርቲያችን ብልጽግና ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ልዩ ትኩረት በመስጠት ችግሩን ለማቃለል ጥረት አድርጓል፡፡ እንደሚታወሰው፤ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ በየአምስት (ስድስት) ዓመታቱ ልዩነት ክለሳ ሊደረግበት የሚገባ ቢሆንም፤ ፖሊሲው ከ20 ዓመታት በላይ ሳይታይ ቆይቷል፡፡

ከብልጽግና በፊት በነበሩ 15 ዓመታት ትኩረት የተሰጠው የትምህርት ማስፋፋት ነበር፡፡ በዚህ ረገድ ብዙ ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡ አዳዲስ የአንደኛ፣ የሁለተኛ ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርስቲዎችና የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋማት ተገንብተዋል፡፡ ሆኖም የተማሪዎች ውጤት ከተመሳሳይ አገሮች ተማሪዎች ጋር ሲነፃፀር ደካማ መሆኑ ታይቷል፡፡ የአገራችን የትምህርት ስርዓት ያመረተው ማንበብ የማይችሉ የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎችን፤ እንዲሁም በሰለጠኑበት መስክ ለሥራ ብቁ ያልሆኑ፤ የችግር ፈቺነት አቅም የሌላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች መሆኑ በተጨባጭ ታይቷል፡፡ ስለዚህ የአገራችን የትምህርት ስርዓት መለያ የጥራት፣ የአካታችነትና የፍትሐዊነት ጉድለት መሆኑ ታይቷል፡፡ 

ቅድመ ብልጽግና የተገኙትን ስኬቶች መነሻ በማድረግ፤ በትምህርት አመራርና አስተዳደር፣ በተደራሽነት፣ በፍትሐዊነት ወዘተ ረገድ የሚታዩ ጉድለቶችን ለማቃለል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በለውጡ ማግስት የማሻሻያ እርምጃ ካደረገባቸው ዘርፎች አንዱ ትምህርት ሥርዓት ነው፡፡ በሂደቱም ፓርቲያችን ትምህርትን ፓለቲካዊ ሳይሆን ሙያዊ፣ ዕውቀትና ክህሎትን የሚጠይቅና ቴክኒካዊ ጉዳይ አድርጎ በማየት ካለፉት የኢትዮጵያ መንግስታት ፍፁም የተለየ አቋም ወስዷል፡፡

ስለዚህ በሥነ ትምህርት ምሁራንና በዘርፉ የረጅም ዘመን ልምድ ባላቸው ምሁራን ተሳትፎ እኤአ ከ2018 እስከ 2030 ዓ.ም የሚተገበር አዲስ የትምህርት ፍኖተ ካርታ እንዲዘጋጅ በማድረግ 8-2-2 የነበረውን ትምህርታዊ መዋቅር ወደ 6-2-4 ስርዓት እንዲቀየር አድርጓል፡፡

ፓርቲያችን በማህበራዊ ዘርፍ የአገራችን ህዝቦች ሁለንተናዊ የማህበራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚሰራ ሲሆን፤ በመጪዎቹ ዓመታት ኢትዮጵያ አገራችንን በሁሉም መስክ አፍሪካዊ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ቆርጦ ተነስቷል፡፡

ስለሆነም፤ በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ቅልጥፍናን እና ውጤታማነትን ለማሻሻል፤ የትምህርት አመራሩንና አስተዳደሩን በማጠናከርና አቅሙን በማጎልበት ብቃትና ውጤታማነቱ እንዲሻሻል የሚያደርግ አሰራር በመዘርጋት በትምህርት ስርዓቱ መልካም አስተዳደር እውን እንዲሆን ይንቀሳቀሳል፡፡  

የግል የትምህርት ዘርፉ ተሳትፎ እንዲነቃቃና ‹‹የትምህርት ልማት ባንክ›› እንዲቋቋም በማድረግ በትምህርት ዘርፍ የሁሉም ባለድርሻዎች አጋርነት እንዲጠናከር ይንቀሳቀሳል፡፡ በሁሉም ደረጃ ያሉ መምህራን የተሻለ ችሎታና ሥነ ምግባር እንዲኖራቸውም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡ በዚህም የመምህርነት ሙያ የሚገባውን ክብር እንዲያገኝ ፓርቲያችን ብልጽግና ጥረት ያደርጋል፡፡ በየደረጃው ያሉ መምህራን የሚያገኙት የሙያ ክፍያና ጥቅማጥቅም እንዲሻሻል በልዩ ሁኔታ ይሰራል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የመካከለኛ ባለሙያዎች መፍለቂያ፤ እንዲሁም በተግባራዊ ስልጠና ብቁ ባለሙያዎች የሚፈጠሩባቸው እንዲሆኑ፤ ከተደራሽነት ጎን ለጎን ለጥራት ትኩረት እንዲሰጡ እና ቴክኖሎጂና ችግር ፈቺ ፈጠራዎች ላይ የሚሰማሩ ወጣቶች ማፍለቂያ  እንዲሆኑ ይሰራል፡፡    

ብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክር የግበረ ገብ ትምህርትን በአንደኛ ደረጃ ስርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲካተት በማድረግ እንዲሁም ተማሪዎች ለማህበረሰቡ የሚሰጡትን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲያጎለብቱ በማድረግ በትምህርት ተቋማትና በማህበረሰቡ መካከል ያለው ግንኙነት እንዲጠናከር፤ በመልካም እሴቶች የታነፁ በሁለንተናዊ ስብዕናቸው ብቁ የሆኑ ዜጎችን ማፍራት የሚችል የትምህርት ስርዓት እንዲኖርም ያደርጋል!

እኛ ብልጽግና ነን!

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *