የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ባዘጋጀው 2ኛ ዙር “ስለኢትዮጵያ” የፖናል ውይይትና የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ ላይ ለመታደም፤ ከፍተኛ የፌዴራል መንግሥት አመራሮች ድሬዳዋ መግባት ጀምረዋል

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ባዘጋጀው 2ኛ ዙር “ስለኢትዮጵያ” የፖናል ውይይትና የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ ላይ ለመታደም፤ ከፍተኛ የፌዴራል መንግሥት አመራሮች ድሬዳዋ መግባት ጀምረዋል። የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ፤ ድሬዳዋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲገቡ፤ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ታደሰ እንዲሁም ሌሎች የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ስለኢትዮጵያ” የተሰኘው የፎቶግራፍ አውደ ርዕይና የፓናል ውይይት በነገው ዕለት በድሬዳዋ ከተማ ይከፈታል። ኢ.ፕ.ድ

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *