በድሬዳዋ አስተዳደር መተግበር በጀመረው “መንገድ ለሰው” ሳምንታዊ ከሞተር ተሽከርካሪዎች ነፃ ቀን መርሀ ግብር ላይ ማሻሻያ ተደረገ

DIRE_PP_PRESS ግንቦት 08/2014

በድሬዳዋ አስተዳደር መተግበር በጀመረው “መንገድ ለሰው” ሳምንታዊ ከሞተር ተሽከርካሪዎች ነፃ ቀን መርሀ ግብር ላይ ማሻሻያ ተደረገ።የድሬዳዋ አስተዳደር በጠራው መድረክ ላይ የተገኙት የሀይማኖት ተቋማት መሪዎችና አባቶች፤ ዘወትር እሁድ ከማለዳው 12:00 እስከ 4:00 እየተተገበረ ባለው መርሀ ግብር ላይ ያላቸውን ቅሬታ እና አስተያየት ለከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ ለሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ አቅርበዋል።የእምነት መሪዎቹ በጥያቄያቸው፤ ሳምንታዊው መርሀ ግብር የአየር ብክለትን እና ራስን ከተለያዩ በሽታዎች ከመከላከል እንዲሁም ጤናን ከመጠበቅ አንፃር፤ ለድሬዳዋ ነዋሪዎች የሚኖረውን ጠቀሜታ እንደሚገነዘቡ ገልፀው፤ ነገር ግን በክርስና እምነት ዘንድ ትልቅ ቦታ በሚሰጣት እለተ እሁድ፤ በከተማው ሙሉ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ በመታገዱና፤ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናትና ምዕመናን የአምልኮ ስርዓት ላይ ችግር ስለፈጠረ ማሻሻያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል።የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በምላሻቸው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የታቀደው የሞተር አልባ እንቅስቃሴ መርሀ ግብር፤ ለነዋሪዎችም ሆነ ለከተማው የሚኖረው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን በማመን ወደ ተግባር መገባቱን ጠቅሰው፤ አስተዳደሩ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር ካለው እጅግ መልካም የስራ ግንኙነትና ቅርበት አንፃር፤ በአምልኮ ስርዓቱ ላይ የተፈጠረውን ችግር አስመልክቶ፤ በተቋምም ሆነ በግለሰብ ደረጃ የቀረበልን ቅሬታም ሆነ ጥያቄ ባለመኖሩ ማሻሻያ ለማድረግ መዘግየታቸውን ገልፀዋል።ከንቲባው አክለውም፤ ጉዳዩን ሆን ተብሎ የክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ ጭቆና ለመፍጠር ታስቦ የተደረገ በማስመሰል፤ ሌላ መልክ እንዲይዝ ለማድረግ የሚጥሩ አካላቶች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ብለው፤ ሳምንታዊው መርሀ ግብር በአብያተ ክርስቲያናቱ የአምልኮ ስርዓት ላይ አሳድሯል የተባለውን አሉታዊ ተጽዕኖ በመገንዘብ፤ ዘወትር እሁድ ከማለዳው 12:00 እስከ ቀኑ 5:00 ድረስ በመሀል ከዚራ ጎዳናዎች ላይ ብቻ እንደሚተገበር መወሰኑን አስታውቀዋል።በድሬዳዋ የሚገኙ ሁሉም የሀይማኖት ተቋማት፤ አስተዳደሩ በሚያከናውናቸው ማንኛውም የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ምዕመናንን በማስተባበር፤ በቀጣይ ጊዜያት ተሳትፏቸውን ይበልጥ እንዲያጠናክሩም ከንቲባ ከድር ጁሀር ጠይቀዋል። በአስተዳደሩ ምክር ቤት የመንግሶት ተጠሪ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በበኩላቸው፤ በአስተዳደሩ የሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚስተዋሉ የአገልግሎት ችግሮችን ለመቅረፍ፤ ከመቼውም ጊዜው በላይ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለድሬዳዋ ቀጣይ እድገትና ልማት የእምነት ተቋማት በሁሉም መስኮች የሚጠበቅባቸውን ማህበራዊ ድርሻ ይወጡ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል ሲል የድሬዳዋ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።በድሬዳዋ አስተዳደር መተግበር በጀመረው “መንገድ ለሰው” ሳምንታዊ ከሞተር ተሽከርካሪዎች ነፃ ቀን መርሀ ግብር ላይ ማሻሻያ ተደረገ።የድሬዳዋ አስተዳደር በጠራው መድረክ ላይ የተገኙት የሀይማኖት ተቋማት መሪዎችና አባቶች፤ ዘወትር እሁድ ከማለዳው 12:00 እስከ 4:00 እየተተገበረ ባለው መርሀ ግብር ላይ ያላቸውን ቅሬታ እና አስተያየት ለከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ ለሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ አቅርበዋል።የእምነት መሪዎቹ በጥያቄያቸው፤ ሳምንታዊው መርሀ ግብር የአየር ብክለትን እና ራስን ከተለያዩ በሽታዎች ከመከላከል እንዲሁም ጤናን ከመጠበቅ አንፃር፤ ለድሬዳዋ ነዋሪዎች የሚኖረውን ጠቀሜታ እንደሚገነዘቡ ገልፀው፤ ነገር ግን በክርስና እምነት ዘንድ ትልቅ ቦታ በሚሰጣት እለተ እሁድ፤ በከተማው ሙሉ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ በመታገዱና፤ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናትና ምዕመናን የአምልኮ ስርዓት ላይ ችግር ስለፈጠረ ማሻሻያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል።የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በምላሻቸው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የታቀደው የሞተር አልባ እንቅስቃሴ መርሀ ግብር፤ ለነዋሪዎችም ሆነ ለከተማው የሚኖረው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን በማመን ወደ ተግባር መገባቱን ጠቅሰው፤ አስተዳደሩ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር ካለው እጅግ መልካም የስራ ግንኙነትና ቅርበት አንፃር፤ በአምልኮ ስርዓቱ ላይ የተፈጠረውን ችግር አስመልክቶ፤ በተቋምም ሆነ በግለሰብ ደረጃ የቀረበልን ቅሬታም ሆነ ጥያቄ ባለመኖሩ ማሻሻያ ለማድረግ መዘግየታቸውን ገልፀዋል።ከንቲባው አክለውም፤ ጉዳዩን ሆን ተብሎ የክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ ጭቆና ለመፍጠር ታስቦ የተደረገ በማስመሰል፤ ሌላ መልክ እንዲይዝ ለማድረግ የሚጥሩ አካላቶች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ብለው፤ ሳምንታዊው መርሀ ግብር በአብያተ ክርስቲያናቱ የአምልኮ ስርዓት ላይ አሳድሯል የተባለውን አሉታዊ ተጽዕኖ በመገንዘብ፤ ዘወትር እሁድ ከማለዳው 12:00 እስከ ቀኑ 5:00 ድረስ በመሀል ከዚራ ጎዳናዎች ላይ ብቻ እንደሚተገበር መወሰኑን አስታውቀዋል።በድሬዳዋ የሚገኙ ሁሉም የሀይማኖት ተቋማት፤ አስተዳደሩ በሚያከናውናቸው ማንኛውም የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ምዕመናንን በማስተባበር፤ በቀጣይ ጊዜያት ተሳትፏቸውን ይበልጥ እንዲያጠናክሩም ከንቲባ ከድር ጁሀር ጠይቀዋል። በአስተዳደሩ ምክር ቤት የመንግሶት ተጠሪ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በበኩላቸው፤ በአስተዳደሩ የሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚስተዋሉ የአገልግሎት ችግሮችን ለመቅረፍ፤ ከመቼውም ጊዜው በላይ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለድሬዳዋ ቀጣይ እድገትና ልማት የእምነት ተቋማት በሁሉም መስኮች የሚጠበቅባቸውን ማህበራዊ ድርሻ ይወጡ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል ሲል የድሬዳዋ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል::

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *