ብልጽግና በህብር እና ትብብር ወደ ስልጣኔ ማማ ያደርሳል

ኢትዮጵያ የበለፀገች ሀገር መሆን አለባት። ኢትዮጵያውያንም የበለጸጉ ህዝቦች ሆነው እንዲኖሩ፤ ለየትኛውም የአለም ሀዝብ የተሰጠው ፀጋ ተችሯቸዋል። ኢትዮጵያም፤ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት፤ የብልጽግና ጉዞን ጀምራለች።

ታታሪ ህዝብ፤ ልዩ የተፈጥሮ ችሮታ፤ የብዝሃ ፈጠራ ባለቤት የሚያደረግ ብዝሃነት ለኢትዮጵያ ልዩ በረከት ነው። ኢትዮጵያውያን፤ለብዙ አመታት ከኖሩበት ድህነት እንዲወጡ፤ የስልጣኔ መዳረሻ መንገዱ ብልጽግና ነው። ብልጽግና ጨለማን ገፎ ብርሃንን ያሰፍናል፤ ብልጽግና ስልጣኔ በኋላ ቀርነት ላይ እንዲሰለጥን ሃያል ክንድ አለው።

ብልጽግና በህብር እና ትብብር ወደ ስልጣኔ ማማ ያደርሳልና ቀጫጭን ሽቦዎች ተሳስረው ብርሃን የሚሰጡበት፤ ጨለማን አሸንፎ ብርሃንን የሚረጨው አምፖልን የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት አድርጓል።

አምፖል ድንቅ የፈጠራ ውጤት፤ አምፖል የትጋት እና ልዩ ሃሳብ ውጤት፤ አምፖል፤ ጨለማን በብርሃን የሚተካ ድንቅ ፈጠራ ነው እና፤ ጨለማ ድህነትን የሚረታ፤ ብርሃን ስልጣኔን የሚያመጣ፤ በኢትዮጵያውያን የትብብር ሃይል፤ በኢትዮጵያውያን ድንቅ የፈጠራ አቅም እና በኢትዮጵያውያን ትጋት፤ ኢትዮጵያውያንን በአዲስ አስተሳሰብና የተግባር አንድነት ወደ ስልጣኔ የሚወሰደው ብልጽግና ፓርቲ፤ አምፖልን ምልክቱ አድርጓል።

ብልፅግናን_ይምረጡ

VoteProsperity

ድሬዳዋ #ኢትዮጵያ

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *