ብልጽግና ፓርቲ ማጠቃለያ ኮንፈረንስ ተካሄደ

#Dire_PP_Press 🇪🇹 ህዳር 19/2014 ዓ.ም

#Dire_PP_Press🇪🇹 ህዳር 19/2014 ዓ.ም የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ማጠቃለያ ኮንፈረንስ ተካሄደ። በድሬዳዋ አስተዳደር በአይነቱ ልዩ እና የመጀመሪያው የሆነው የብልጽግና ፓርቲ ኮንፈረንስ በህሊና ጸሎት የተጀመረው የዝግጅት ምዕራፍ ማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል። በመክፈቻ ንግግር መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከውስጥና ከውጭ የጥፋት ሃይሎች ህልውናዋን የሚፈታተን አደጋ ገጥሟት አሸንፋ ለመውጣት እና አንድነቷን ለማስጠበቅ እና ሊያፈርሷት የተማማሉ ሀይሎችን በዜጎቿ የተባበረ ክንድ አፍርሳና ቀብራ የሀገርን ሉአላዊነት ለማስከበር መላው ህዝባችንና የፓርቲያችን አመራሮችና አባላት ቀፎው እንደተነካበት ንብ የሚጠበቅብንን ኃላፊነት ልንወጣ ይገባል ብለዋል። አክለውም ፓርቲያችን ተጨባጭ ተግባርን እና የየወቅቱን ሁኔታውን ማዕከል ያደረገ የአመራር የመገነባቢያ መድረኮች በማዘጋጀት ውስጣዊ ችግሮችን በራስ አካሄድ ለማረምና መልሶ የማደራጀት ስራዎች በውጤታማነት መከናወኑን ገልጸዋል። በሀገራችን የተከፈተው ጦርነት በምዕራባውያን አገራት የሀገራችን ህዝቦችን ታሪካዊ የነፃነት መንፈስ በመስበር ደካማና የተበታተነች እና ሉአላዊነቷ የተነጠቀች ሀገር ለመፍጠር የሚደረግ ጦርነት የአስተዳደራችን አመራሮችና ህዝባችንም ‹‹ተከተሉኝ›› ብለው ወደ ጦር ሜዳ ያቀኑትን የመሪአችን ጥሪ ተቀብለን የምንችል በግንባር ከፊላችን ደግሞ በደጀን ቆመን የአድዋን ድል በመድገም አዲስ ታሪክ ለመስራት ሌት ተቀን የምሰራበት ወቅት ላይ እንገኛለን ሲሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ገልጸዋል። በመቀጠልም ከንቲባችን አመራሮቻችንና ወጣቶቻችን በሚደያ ግንባር ለተከፈተንብን የስነ ልቡና ጦርነት ‹‹ dis information ›› በቃን ብለን የውሸት መረጃቸውና ሴራቸውን በማወቅና በማጋለጥ ተግተን ከሰራን ጠላቶቻችንን እናሸንፋለን፡፡ ከመሪያችን ዶ/ር አቢይ አህመድ ጎን ተሰልፈናል። ብለዋል። የፓርቲው ጽ/ቤት ም/ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻኪር አህመድ የፓርቲው የሩብ አመት አፈጻጸምና የቀጣይ ሩብ አመት እቅድ ያቀረቡ ሲሆን በሰነዶቹ የአስተዳደሩ የፓርቲ ስራዎችና የልማት ስራዎች በማጣጣም የተሰሩና በቀጣይም ተጠናክረው ለማስቀጠል በተገኘው ድል በቀጣይ ፓርቲያችን አገራችንን ወደሚገባት ብልጽግና ለማሻገር ባገኘነው ታሪካዊ ሀላፊነት የአዲስ ምዕራፍ ጉዞ መጀመሩን ገልጸዋል። በመርሀ ግብሩ የፓርቲው የኦዲት ኮሚሽን አፈጻጸም ሪፖርት እና የቀጣይ ምዕራፍ እቅድ የቀረበ ሲሆን ኮሚሽኑ የተሰጠውን ኃላፊነትን መሰረት በማድረግ የፓርቲው ጠንካራ ክንፍም እንደሚሆን የፓርቲው ኦዲት ኮሚሽነር ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን ጠቅሰዋል። በመጨረሻም በቀረቡት ሰነዶች ውይይት በማድረግ እና የተለያዩ የውሳኔ ሀሳቦች የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ኮንፈረንሱ ተጠናቅቋል።

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *