የነገውን ብሩህ ዘመን ለማየት ፣ የብልፅግና ማዕዱን ለመቋደስ አልጓጉም?

ማዕዱ ምንድነው ካሉን የብልፅግና ማዕዱ ለሁሉም ዜጎችዋ የምትስማማ፣ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን የምትመስል፣ የበለፀገች፣ የብሔሮችን መብት ከግለሰብ መብቶች ጋር አጣጥማ የምታስጠብቅ፣ ጠንካራ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ መገንባት ነው፡፡

ማዕዱ ምንድነው ካሉን የብልፅግና ማዕዱ ከምግብ ዋስትና ጥያቄ የተሻገረ የዜጎችን የምርጫ አድማስ የሚያሰፋ የበለፀገ ኢኮኖሚ መገንባት ነው!

ብልፅግና ፓርቲ ያቀረበው ማዕድ ዜጎችን በዛሬ ድህነት ውስጥ ሳይሆን ነገ በተሻለ ሁኔታ ፍላጎታቸው ተሟልቶላቸውና ጥራት ያለው ኑሮ እንዲኖሩ ማድረግ ነው!

እንግዲያውስ እስከ ሚያዝያ 15 ቀን ብቻ የሚቆየውን የምርጫ ካርድ መስጫ ቀን ተጠቅመው ጊዜ ሳያጠፉ የምርጫ ካርድዎን በመውሰድ የብልፅግና ማዕዱን አትረፍርፎ ያቀረበውን የበራ አምፖል ልዩ ምልክቱ ያደረገውን ብልፅግና ፓርቲን ይምረጡ!

Loading

One thought on “የነገውን ብሩህ ዘመን ለማየት ፣ የብልፅግና ማዕዱን ለመቋደስ አልጓጉም?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *