የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ የማጠቃለያ የምርጫ ቅስቀሳ መርኀግብር በድምቀት ተካሄደ።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከየካቲት 8 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅቶች ነበሩ። ግንቦት 28 ይደረጋል በተባለው ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳው የሚያበቃው በግንቦት 23 ነበር። ሆኖም ምርጫው ወደ ሰኔ 14 መዛወሩን ተከትሎ የምርጫ ቅስቀሳውም አብሮ መራዘሙ ይታወሳል። የምርጫ ቅስቀሳው ከመጭው አርብ በፊት ተጠናቆ ምንም ቅስቀሳ ወደማይካሄድበት ወደ የጥሞና ጊዜ ለመግባት የዛሬዋ እሁድና ጥቂት ቀናት ቀርተዋል። በዚሁ መሠረት በአስተዳደሩ ከተማና ገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች በቅስቀሳ ማጠቃለያው ላይ በመገኘት ለፓርቲው ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል። የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ ፓርቲያችን ብልጽግና የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን ፓርቲ ነው፣ ከሁሉም በሁሉም ለሁሉም የሆነ ”ህብረብሄራዊ ወንድማማቾችነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መርህ ላይ የቆመ የኢትዮጵያ ህዝቦች ፓርቲ ነው፣ አክለውም የፓርቲው ምልክት የሆነው ብርሃን ባለበት ጭለማ አይቆምም ብለዋል። የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ ለፓርቲ ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ፓርቲው በጽናት እየሰራ ተጉዞ በበርካታ ፈተናዎችና ውጣውረዶች ተፈትኖ በጥንካሬ ከግብ የደረሰ ፓርቲ መሆኑን ገልጸው የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ብልጽግናን እንዲመርጡ ጠይቀዋል። ሁለቱ ድሬዳዋን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት እጩ የሆኑት አቶ አብዱልጀዋድ መሀመድ እና ዶ/ር ቢፍቱ መሀመድ ራሳቸውን አስተዋውቀው የሚበራ አምፖልን እንዲመርጡ ጠይቀዋል። በድሬዳዋ ታሪክ የመጀመሪያዋ የተወካዮች ምክር ቤት ሴት እጩ የሆነችው ዶ/ር ቢፍቱ መሀመድ የህዝባችን የብልጽግና፣ የሰላምና የደስታ ዘመን በእጅጉ ለማፋጠን በወንድማማችነትና በእህትማማችነት መንፈስ በጋራ በመቆም ኃላፊነታችንን እንወጣ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። በመጨረሻ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር የእለቱ መርኃግብር ተጠናቀቀ።

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *