prosperity menifesto

የምርጫ 2013 የብልጽግና ፓርቲ ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ይፋዊ የእውቅና መድረክ ተካሄደ

“ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የምርጫ 2013 የብልጽግና ፓርቲ ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ይፋዊ የእውቅና መድረክ በሸራተን አዲስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የዕውቅና መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ የከፈቱት የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ብናልፍ አንዷለም ፓርቲያችን ብልጽግና የአገራችንንና አለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በጥልቀት የገመገመ፣አገራችንን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በውል ለይቶ ትክክለኛ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ያስቀመጠ፣ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝቦች በእኩል አካቶና አቅፎ የማታገያ ሜዳ ያመቻቸ፣በሚሊዬን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን በአባልነትና በደጋፊነት ከጎኑ ያሰለፈ፣በለውጥ ውስጥ የተወለደ፣ለለውጥ የሚተጋ፣የተስፋ ብርሐን የሰነቀ የዛሬና የነገ ፓርቲ ነው ብለዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝደንት ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ፓርቲው በምርጫ ወቅት የሚጠቀምበትን ማኒፌስቶና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክትን ይፋ አድርገዋል፡፡በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝደንት ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድን ጨምሮ በርካታ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *