ሀገራዊና ጂኦ-ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር በማድረግ፣ ከብልጽግና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተላለፈ መልእክት

የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ልጆች፣የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ክቡራትና ክቡራን፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትገኝበት ጂኦ ፖለቲካዊ ከባቢ ዛሬም እንደ ትናንቱ የዓለም ዓይን ማረፊያ ሆኖ ይገኛል። ከሜዲትራንያን ባሕር ቀጥሎ በዓለም ታሪክ ላይ በሚደረጉ የንግድና ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች የሚጠቀሰው ቀይ ባሕር ነው። በዚህ ቀጣና ላይ የበላይነት መያዝ በዓለም አቀፍ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ይታመናል። እናም ብዙ ሀገራት ከሌላ የዓለም ዳርቻ
Read More

ግድቡ ኢትዮጵያ ሃብቷን በራሷ አቅም አልምታ ችግሮቿን መፍታት እንደምትችል የምታሳይበት ነው … ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ

ግድቡ ኢትዮጵያ ሃብቷን በራሷ አቅም አልምታ ችግሮቿን መፍታት እንደምትችል የምታሳይበት ነው … ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ሃብቷን በራሷ አቅም አልምታ ችግሮቿን መፍታት እንደምትችል የምታሳይበት ፕሮጀክት ነው ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ገለጹ። ዶክተር ቢቂላ በኢትዮጵያ እየተገነቡ በሚገኙ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ዜጎች ንቁ ተሳትፎ እንድያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ
Read More

የትምህርቱ ዘርፍ ችግሮቻችን በብልጽግና ይፈታሉ

ከኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት ከፍተኛ ሀብት ሲመደብለት የቆየው የትምህርት ዘርፍ፤ ከፍተኛ የጥራትና የተደራሽነት ችግር የሚታይበት በመሆኑ ፓርቲያችን ብልጽግና ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ልዩ ትኩረት በመስጠት ችግሩን ለማቃለል ጥረት አድርጓል፡፡ እንደሚታወሰው፤ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ በየአምስት (ስድስት) ዓመታቱ ልዩነት ክለሳ ሊደረግበት የሚገባ ቢሆንም፤ ፖሊሲው ከ20 ዓመታት በላይ ሳይታይ ቆይቷል፡፡ ከብልጽግና በፊት በነበሩ 15 ዓመታት ትኩረት የተሰጠው የትምህርት ማስፋፋት ነበር፡፡
Read More

ለወጣቱ ልዩ ትኩረት የሰጠው ብልጽግና!

ወጣትነት- በአካል የጠነከረ፣ በመንፈስ የቀደመ፣ ለውጤት የቸኮለ እምቅ አቅም ያለው ኃይል ነው። ይህን ኃይል በተደራጀና በተገቢ መንገድ ከተመራ ስኬትን ማጣጣም እንደሚቻል ብልጽግና ፓርቲ በጽኑ ያምናል። ወጣቶችን የስራዎቹ ሁሉ ማዕከል አድርጎ ያያቸዋል፤ ለጠንካራ አገር ግንባታ መሰረት መሆናቸውን ይቀበላል። በመሰረቱ ወጣቶች ለዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ ፈተናዎች እንዳሉባቸው ብልጽግና ይረዳል። ተምረው ስራ ማጣት፣ ስራ ቢቀጠሩም በቂ ገቢ ያለማግኘት፣ ለስራ
Read More

ብልጽግናና መልካም እሴቶች አይነጣጠሉም!!

ኢትዮጵያውያን በዘመናት ውስጥ እርስ በርስ ተሳስረዋል፤ በጠበቀ ማንነት ተጋምደዋል። በዓለም ዘንድ ታላቅ በሚያደርጋቸው እነርሱነታቸው ተሰናስነዋልም። የእነርሱ ጥብቅ መተሳሰር የመጣው በዘመናት ሂደት ነው። ለዚህ የተለያዩ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል። በዘመናት ውስጥ ደማቸውን ቀለም፣ አጥንታቸውን ብዕር አድርገው የጻፉትን መልካም ታሪክ ዋቢ ማድረግ እንደሚቻል ብልጽግና ፓርቲ ያምናል። በብልጽግና አተያይ ኢትዮጵያውያን ከውጭ የመጣን ጠላት ለመከላከል፣ ለማጥቃትና የጋራ ክብራቸው እንዳይገሰስ ለማድረግ
Read More

ብልጽግና ቃሉ ተግባር የሆነ ፓርቲ!

ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ያደሩ የቤት ስራዎቸ አሉ። እነዚህን ለይቶና በቅደም ተከተል አቅዶ የመተግበር አስፈላጊነት አጠያያቂ አይሆንም። ለዚህም ነው ፖለቲካው ሲታመም የተገራገጨውን ኢኮኖሚና ለዓመታት ሲንከባለል የመጣው ማህበራዊ ቀውስ በፍጥነት ታቅዶ መስመር ካልያዘ ለአገር አደገኛ መሆኑን የለውጥ ኃይሉ በመገንዘብ ጊዜ ሳይወስድ አፋጣኝ መፍትሄ የሰጠው። ስለሆነም የለውጥ ኃይሉ ሁሉንም ለመፍታት ማቀድ፣ ያቀዱትን ተግባራዊ ለማደረግ መንቀሳቀሱን ቀዳሚ ተግባሩ አደረገ።
Read More

ሩቅ አስቦ – ሩቅ ለመጓዝ የተነሳው ብልጽግና!

ኢትዮጵያ በሥነ ፈለክ ምርምር መስክ ተጠቃሽ አገር ነች፡፡ ይህን የአገራችንን ሁኔታ የተገነዘበው የዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚ ህብረት፤ በ2011 ዓ.ም በአንድሮሜዳ ህብረ ኮከብ ውስጥ የሚገኙትን አንድ ኮከብና አንድ ኤክሶ  ፕላኔት ኢትዮጵያ እንድትሰይም ዕድል ሰጥቶ ነበር፡፡ ስለዚህ አገራችን በህዋ ሳይንስ ዘርፍ ያላት ተሳትፎ አሁን በሚገኝበት ደረጃ መሆኑ የሚያስቆጨን ቢሆንም፤ ለቴክኖሎጂው ዘርፍ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ፓርቲያችን ከተመሠረተ ወዲህ አገራችን
Read More

ብልጽግና – ለዜጎች ክብር የሚሰራ ፓርቲ!

ዜጎቿን ያላከበረች አገር በሌሎች ልትከበርና ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ ሊኖር አይችልም፤ ዜጎቿን በሁለንተናዊ መልኩ ማክበር የቻለች አገር ግን ለዜጎቿ በሰጠችው ክብር ልክ ከፍ ብላ ትታያለች፣ ሉዓላዊነቷም ተከብሮ ትኖራለች፡፡ አገር ዜጎቿን ትመስላለች የሚባለውም ለዚህ ነው፤ ዜጎችም የአገራቸው ገጽታዎች ናቸውና!! ብልጽግና ፓርቲ በመደመር መስመር መዳረሻውን በሁለንተናዊ ብልጽግና ለማሳካት ጉዞ የጀመረው የዜጎችን ክብር በማስቀደም ነው፡፡ ብልጽግና የዜጎች ወይም ሰዎች ክብር
Read More

ህዝብን የሚመጥን የትራንስፖርት መሰረተ ልማትን እውን የማድረግ የብልጽግና መሰረታዊ ርዕይ!

የትራንስፖርት ዘርፍ በአገራችን ዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር ከተገነባበት ጊዜ ጀምሮ ያለና ረዘም ያለ ጊዜ ከወሰዱ መንግስታዊ ተቋማት የሚመደብ ነው፡፡ ይህ የረጅም ዕድሜ ባለቤትና የዕድገት መሰረት ዘርፍ ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ግልጽ የትራንስፖርት ዘርፍ ፖሊሲ አልነበረውም፡፡ በዚህም የተነሳ ለህዝባችንና ለአገራችን የሚመጥን የዘመነ ትራንስፖርት መሰረተ ልማትን ከማድረስና ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር ሰፊ ጉድለት ታይቶበታል። ብልጽግና ፓርቲ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ባሳለፋቸው
Read More

“የብልጽግና ጉዞ” – አስታራቂ ትርክት ፍለጋ!!

ባለፉት ሦስት ዓመታት አዲስ ዓይነት የፖለቲካ ትርክት ብቅ ብሏል። የብልጽግና ትርክት። ሀገራችን በአንድነት ጸንታ እንድትቆይ ብቻ ሳይሆን፣ የግለሰቦች ነጻነትና የቡድኖች እኩልነት የወንድማማች እሴትን አቅፈው እንዲተገበሩ የሚሻ ዓይነት ትርክት ነው። ከእኩልነትና ከነጻነት ተቃርኖ የተወለዱት የዘመናት የፖለቲካ ችግሮቻችን በዴሞክራሲና በወንድማማችነት እሴት ባለመደገፋቸው የተባባሱ ናቸው ብሎ ብልጽግና ያምናል። ከዚህ ቀደም የተፈጠሩ ትርክቶች አስታራቂና የኢትዮጵያን ችግሮች በምሉዕ እይታ ያልዳሰሱ
Read More