በጎነት ለኢትዮጰያ ከፍታ’

በድሬዳዋ አስተዳደር ”በጎነት ለኢትዮጰያ ከፍታ” በሚል መርህ ሲከናወን የቆየው የክረምት በጎ ፍቃድ ተግባራት የማጠቃለያ የምስጋና እና የእውቅና መርሀ – ግብር የፊታችን እሮብ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል። በዚህ በጎ ተግባር የተሳተፉ ተቋማት እና ግለሰቦችን ድሬ ከልብ ታመሰግናለች።
Read More

“ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሀሳብ በ10 የስልጠና ማዕከላት ለ12 ቀናት ሲሰጥ የቆየው 2ኛ ዙር የከፍተኛ እና የመካከለኛ አመራሮች የስልጠና መድረክ በሁሉም ማዕከላት በዛሬው እለት ተጠናቋል።

ጥቅምት 11 ቀን 2016 #DIREPROSPERITY “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሀሳብ በ10 የስልጠና ማዕከላት ለ12 ቀናት ሲሰጥ የቆየው 2ኛ ዙር የከፍተኛ እና የመካከለኛ አመራሮች የስልጠና መድረክ በሁሉም ማዕከላት በዛሬው እለት ተጠናቋል። የስልጠና መርሀ ግብሩ ፓርቲያችን በምርጫ ማግስት ለህዝብ ቃል የገባቸውን ጉዳዮች በተሳካ ሁኔታ ለመፈፀም አቅም የሚያዳብርበት፣ አመራሩ ውስጣዊ አንድነቱን አጠናክሮ ለቀጣይ ሀገራዊ ተልእኮ በታላቅ ተነሳሽነት
Read More

የፓርቲያችንን ተልዕኮ ተቀናጅተን በመፈፀም ኢትዮጵያን በጋራ እናበለፅጋለን!

የፓርቲያችንን ተልዕኮ ተቀናጅተን በመፈፀም ኢትዮጵያን በጋራ እናበለፅጋለን! ህብረ-ብሔራዊነት ጌጣችንም ሀይላችንም ነው።ብዝሀነቶቻችን እዳዎቻችን ሳይሆኑ ፀጋዎቻችንና ሀብቶቻችን ናቸው። የጠነከረ አንድነት ደግሞ አብሮ ችግሮችን የማለፍ፣ የማደግ እና የመበልፀግ ቁልፋችን ነው። በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የምንገኝ አመራር እና አባላት ወንድማማችነታችንን እና እህትማማችነታችንን እያጠናከርን ታፍራና ተከብራ ዘላለም የምትኖር ህብረብሔራዊት ኢትዮጵያን የማፅናትና ሁለንተናዊ ብልፅግና የማረጋገጥ ራዕይ ሰንቀን በጋራ የምንገሰግስ የብልፅግና ቤተሰቦች ነን።
Read More