ብልፅግና በኩራት የሚመርጡት የእርስዎ ፓርቲ ነው!

ብልፅግና በህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነት ኢትዮጵያን የሚያሻግርና ዜጎች በኩራት የሚመርጡት የሁሉም ፓርቲ ለመሆን ያስቻሉ የሚታዩ ተጨባጭ የእስካሁን ድሎች ባለቤት ነው፡፡

ብልፅግና በቀጣይም የእስካሁን ጥንካሬዎችንና የለውጡን ዘርፈ ብዙ ድሎች በተሻለ መደላድል አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደተወዳዳሪ ፓርቲ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ አሸናፊ ለመሆን የተሻለ ሃሳብ በማፍለቅ ጎልቶ የሚታይ የፖለቲካ ቁመና ያለው ፓርቲ ነው፡፡

ሁሉንም ዜጎች አቃፊና አሳታፊ ሆኖ የቀረበው ብልፅግና መላ ኢትዮጵያዊያን ያለአንዳች ልዩነትና ገደብ በእኩልነትና በፍትሃዊነት የተሻለ ተጠቃሚ መሆን የሚያስችላቸው ስኬት ባለቤቶች በመሆን የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እንዲያደርጉ የሚያስችል ተወዳዳሪና ተመራጭ የሚሆን አሻጋሪ ሃሳቦች ያሉት ፓርቲ ነው፡፡

ብልፅግና እንደአንድ የህዝብ ፓርቲ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ካለው ከፍተኛ ፍላጎትና ፅኑ እምነት ባሻገር ኢትዮጵያና ዜጎቿ ተገቢው ክብር ይገባቸዋል ብሎ ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጥም ነው፡፡

በመሆኑ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከይስሙላ ዴሞክራሲና ምርጫ ተላቃ እውነተኛና ዜጎች በነፃነት ያሻቸውን የሚርጡበት ምርጫ ተግባራዊ እንዲሆን ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ገና ከጅምሩ የፖለቲካ ምህዳሩን ያለገደብ እንዲሰፋ አድረጓል፡፡

በዚህም ሁሉንም ተሳታፊ ያደረገ ሀገራዊ የፖለቲካ ምህዳር  እና በገለልተኛና ነፃ ተቋማት የሚዳኝ ምርጫ አስፈላጊነት ታምኖበት ወደ ተግባር መሸጋገር ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራችንና የሀገረ መንግስት ግንባታችን ከነበረበትና የፖለቲካ ስልጣንን ማቆያ መሳሪያ ተደርጎ የጋራ እሴቶችን ከሚንድና የበዳይ ተበዳይ ትርክት ቅኝት ተላቆ አሁን ላይ በአዲስ ቅኝት የህዝቦችን አንድነትና የጋራ እሴትን ማጎልበት በሚያስችልና ወደ ብልፅግና በሚያደርስ የከፍታ መንገድ ተተክቷል፡፡ እስካሁንም ይህ አዲስ የከፍታ መንገድ በመደመር እሳቤ መላ ዜጎችን አቅፎና አሳትፎ እየተሰራ በርካታ ፖለቲካዊ ብልሽቶችን እየቀረፈና ድሎችን እያመጣ ይገኛል፡፡

እንደሀገር ያሉብን ለረጅም ጊዜያት እያደጉና እየተወሳሰቡ የመጡ ያከማቸናቸውን በርካታ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችንና ተግዳሮቶችን መንስኤ ፍለጋ በመኳተን ታሪካዊና አሁናዊ ባለቤት እያሸከሙ በትችትና በእርግማን ጋጋታ መሸሽ እንደማይገባ የፓርቲያችን እምነት ነው፡፡

እንዲሁም በኋላቀርና በተቸከለ አስተሳሰብ በማያሻግር ጥገናዊ ለውጥ ባሉበት ለማፅናት በቀድሞ አገዛዝ የነበረው ፖለቲካዊ ፍላጎትና ትግበራ በፍጥነት መቆም እንዳለበት ብልፅግና ፓርቲ በሚገባ ተረድቶ ይህንኑ ለማስቀረት የሚያስችል የለውጥ እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡

ይህ ትውልድ ብልፅግና ከመነፈግ አልፎ ለቀጣዩም ውዝፍ እዳን አውራሽ እንዲሆንና የቀደመው ትውልድ የተጎናፀፋቸው በርካታ አኩሪ ሀገራዊ ድሎቹ በጥቂት አሉታዊ ጎዶሎዎች ታሪኩ እየደበዘዘ እንዲቀጥል ብልፅግና አንዳችም ፍላጎት የሌለውና አምርሮ የሚታገል ፓርቲ ነው፡፡ 

ብልፅግና ፓርቲ ዘርፈ ብዙ ሀገራዊ ችግሮቻችንን በሚገባ ተረድቶ የመውጪያ በራቸውን የሚከፍት በእርግጥም ለኢትዮጵያዊያን ብልፅግና ይገባቸዋል ብሎ በፅኑ የሚያምንና ለብልፅግናቸው ስኬትም ከጅምሩ አንስቶ በስራ ላይ የሚገኝ ፓርቲ ነው፡፡

ፓርቲያችን በርካታ ሀገር በቀልና አሻጋሪ የለውጥ እርምጃዎችን ተቋማዊ መሰረት እንዲኖራቸው በማድረግ የሚተጋ በአዲስና በላቀ አስተሳሰብ የቀረበ የኢትዮጵያዊያን ፓርቲ ነው፡፡ ብልፅግናን መምረጥ ኢትዮጵያን ማበልፀግ በመሆኑ በኩራት የሚመርጡት የእርስዎ ፓርቲ ነው፡፡

#ብልፅግናን_ይምረጡ

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *