ለወጣቱ ልዩ ትኩረት የሰጠው ብልጽግና!

ወጣትነት- በአካል የጠነከረ፣ በመንፈስ የቀደመ፣ ለውጤት የቸኮለ እምቅ አቅም ያለው ኃይል ነው። ይህን ኃይል በተደራጀና በተገቢ መንገድ ከተመራ ስኬትን ማጣጣም እንደሚቻል ብልጽግና ፓርቲ በጽኑ ያምናል። ወጣቶችን የስራዎቹ ሁሉ ማዕከል አድርጎ ያያቸዋል፤ ለጠንካራ አገር ግንባታ መሰረት መሆናቸውን ይቀበላል።

በመሰረቱ ወጣቶች ለዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ ፈተናዎች እንዳሉባቸው ብልጽግና ይረዳል። ተምረው ስራ ማጣት፣ ስራ ቢቀጠሩም በቂ ገቢ ያለማግኘት፣ ለስራ ፍለጋ ከአካባቢያቸው እርቀው በመውጣታቸው የቤት ችግር የሚፈታተናቸው መሆን፣ አዲስ ህይወት የመመስረት ፍላጎት ቢኖራቸውም እርሱን የሚያሟሉበት መንገድ አለመኖር ከችግሮቻቸው መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን ብልጽግና በአጽንኦት ይገነዘባል።

በአገር የኢኮኖሚ ለውጥ ላይ ከፍተኛ አቅም የሆነው ኃይል በእንደዚህ ዓይነት ችግሮች ተተብትቦ የሚፈለገውን አገራዊ ዕድገት ለማስመዝገብ እንደሚያዳግት፣ በነዋይ የማይተመን ሀብት እንደሚባክንና ታላቅ ኪሳራ እንደሆነም ፓርቲያችን ብልጽግና አሳምሮ ይረዳል። ለዚህም ነው ብልጽግና ወጣቱን ኃይል በአግባቡ በመምራት የስራዎች ሁሉ ማዕከል ለማድረግ ቁርጠኛ የሆነው።

ፓርቲያችን የወጣቶችን ጉዳይ ጊዜያዊ የፓለቲካ ትርፍ ለማግኘት ብቻ የሚያቀነቅነው ጉዳይ አይደለም። ጠንካራ አገርና አገረ መንግስት ለመመስረት ከሚደረገው ራዕይ የሚመነጭ እውነት እንጂ! ይህን እውን ለማድረግ ደግሞ ወጣቶችን በሁሉም ዕድገት ዘርፎች በማሳተፍ ለውጥ ለማምጣት በልዩ ትኩረት ይሰራል። እምቅ አቅማቸውንና ችሎታቸውን በመጠቀም ከራስ እስከ አገር ለመቀየር የሚችሉ የጠንካራ አገር ግንባታ የማዕዘን ድንጋይ መሆናቸውን በማመን ለውጤታማነቱ ፓርቲያችን ተግቶ ይሰራል። ብልጽና ወጣ የነበር ጣት ነው የሚለውን ብሂል የሚገነዘበው እንደተራ ነገር አይደለም። ይህ ኃይል በተፈላጊው አገራዊ እሴት ተገንብቶ ካደገ፣ በቂ ትኩረት ከተሰጠውና ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረለት አገርን ወደልዕልና የሚያሻግር ተኪ የሌለው ኃይል መሆኑን በመገንዘብ እንጂ!

ለወጣቱ ትኩረት አለመስጠትና ይህን ኃይል አለመጠቀም ማለት የአገር ዕድገትን የኋልዮሽ መጎተትና የአገር ተስፋን ማምከን መሆኑንም ብልጽግና በልዩ ሁኔታ ይገነዘባል። ስለሆነም የነገዋ ኢትዮጵያ ተረካቢዎችና የዛሬዋ ኢትዮጵያ አፍላ ጉልበቶች የሆኑ ወጣቶች ኢትዮጵያዊ እሴትን ተላብሰው እንዲያድጉና የሚማሩበት፣ የሚኖሩበትና ከዚያም አለፍ ሲል ዘና የሚሉበት ምቹ ሁኔታ መፈጠር እንዳለብትም አጽንኦት ይሰጣል። ለዚህም ሲባል ነው መዲናችን አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ አገሪቱ ወጣቶችን ማዕከል ያደረጉ የመማሪያ የመዝናኛና የንባብ ማዕከላትን በልዩ ትኩረት እየገናባና ለፍሬ እያበቃ የሚገኘው።

እነዚህን ማድረግ ተራ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን አገርን የማጠንከርና ብልጽግናዋን እውን የማድረግ መሰረት መሆኑንም በትልቁ ይረዳል። ብልጽግና ወጣቶች አገር ተረካቢዎች ብቻ ሳይሆኑ የአገር ባለቤት እንዲሆኑ፤ የዜግነት ሚናቸውን እንዲወጡ፣ እምቅ አቅማቸውንና ችሎታቸውን ያለምንም እንቅፋት ተግባር ላይ እንዲያውሉ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን በመቀየስ አገራዊ ጠቀሜታቸውን ያጎለብታል። የወጣቶች እምቅ የፈጠራ ችሎታ በተግባር ላይ እንዲውልና ለኢትዮጵያ ብልጽግና ወሳኝ ግብዓት እንዲሆንም ልዩ ትኩረት በመስጠት ይንቀሳቀሳል።    

ብልጽግና ወጣቶችን “የአገር ባለቤት እናደርጋለን” ሲል ደግሞ፣ ለመጪው ትውልድ የተመቸች ኢትዮጵያን ለመፍጠር አሁን ወጣቶች በአገራቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የተሳታፊነትና የተጠቃሚነት ብቻ ሳይሆን የመሪነትና የወሳኝነት ሚናቸው ከፍተኛ እንዲሆን አበክሮ ይሰራል ማለት ነው።

ፓርቲያችን ወጣቶችን በሁሉም የአመራር ደረጃ ላይ እንዲሳተፉ ያደርጋል። በሁሉም የፖሊሲዎች ማጠንጠኛ ሀሳቦች ላይ የወጣቶች ጉዳዮች ማዕከል ይሆናሉ። ይህም የአገራችን ወጣቶች አገር ተረካቢዎች ብቻ ሳይሆኑ ባለቤትም እንዲሆኑ በቁርጠኝነት የመስራት የቃል ኪዳን ማሰሪያ ነጥብ ነው።  ባለፉት ሶስት ዓመታት ብልጽግና ወጣቶችን በመሪነት ቦታ ማምጣቱን ለዚህ ጉዳይ በዋቢነት መጥቀስ ይቻላል።

ሌላው ነጥብ ወጣቶች ምክንያታዊ አስተሳሰብ እንዲያዳብሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነና የሚያከናውን መሆኑ ነው። ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ፣ ሁለንተናዊ ሰብዕናቸው ጤናማ እንዲሆን፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ፣ የስራ ፈጣሪነት አስተሳሰብ እንዲያሰርጹና ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የሚያደርጓቸውን ስራዎች በጽኑ አቋም እያከናወነ ነው፤ ያከናውናልም።

ብልጽግና የብድር አገልግሎት ሥርዓት በመዘርጋት ወጣቶች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር ተግባራዊ ያደርጋል። በተጨማሪም ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በሚፈጠሩ የስራ እድሎች ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ሰፋፊ አገራዊ ፕሮግራሞች ይዘረጋል።

የወጣቶች አቅም ማጎልበት ላይ ትኩረት ያደረገ ስራዎችን በማከናወን እምቅ አቅማቸውን በተግባር ላይ እንዲያውሉት ከማድረግ ባሻገር ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ፣ በሁሉም ዘርፎች ተሳታፊነታቸው እንዲጠናከር፣ ተወዳዳሪነታቸው እንዲጨምር በጽናት ይሰራል። ለዚህም ወጣቶች አጠቃላይ መረጃዎችን በትክክለኛው ሰዓትና በትክክለኛው ቦታ እንዲያገኙ ያደርጋል።

ምክንያቱም ወጣቶች ዛሬ ላይ በመረጃ ክፍተት ምክንያት አገራዊም ሆነ አህጉራዊ መረጃዎቻቸው ተዛብተው ምልከታቸውን እያዛቡ፤ ጉዟቸውንም እያዛነፉባቸው ይገኛል፡፡ የዚህ ዓይነቱን ችግር ለመፍታት ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች የግንኙነትና የመረጃ ማዕከል (ዪዝ ኮኔክት ፕሮግራም) በመተግበር ወጣቶች ከአፍሪካና ዓለምአቀፍ አቻዎቻቸው ጋር ትስስር የሚፈጥሩበት እድል ያመቻቻል። ይሄም በሁሉም አቅጣጫ ትክክለኛ መረጃ በትክክለኛው ጊዜና ቦታ እንዲያገኙ፣ በምክንያታዊነት ነገሮችን እንዲመረምሩ እድል ይፈጥርላቸዋል።

እነዚህን ስራዎችም ለማጠናከር፣ የውክልናና የመሪነታቸውን ሚና እንዲጫወቱ ለማድረግ የሚያስችል አገር አቀፍ የወጣቶች ካውንስል እንዱቋቋም ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። ይህም ወጣቶች በአገራቸው ላይ የማይተካ ሚናቸውን እንዲጫወቱ ያደርጋቸዋል። ወጣቶች ለብልጽግና ድምጻቸውን ይስጡ የምንለውም ለዚሁ ነው!

እኛ ብልጽግናዎች ነን!

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *