ህዳር 21/2014 ዓ.ም የተከበራችሁ የድሬዳዋ ነዋሪዎች:-

የተከበራችሁ የድሬዳዋ ነዋሪዎች:-ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት ከእኛ ይጠበቃልና፤ እኔም ከሌሎች ወንድሞቼ ጋር ወደ ትግሉ ሜዳ ለመዝመት ተዘጋጅቻለሁ። በግንባር ተገኝተን ያዘጋጀነውን ስንቅ እናቀብላለን፤ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ጀግናው ሠራዊታችንን በወኔ እናበረታታለን። የአስተዳደራችን የፀጥታ ኀይሎችና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችም፤ ከመቼውም ጊዜ በላይ የድሬዳዋን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ፤ የልማትና አስተዳደራዊ ሥራዎችን በሙሉ አቅማቸው ለማከናወን ተዘጋጅተዋል። መላው ነዋሪዎች አካባቢያችሁን በመጠበቅ፤ ሠራዊቱን በመደገፍና፤ ወደ ግንባር በመዝመት፤ እንዲሁም በፀሎት ከጎናችን እንድትሆኑ ጥሪ አቀርባለሁ። ያለጥርጥር ኢትዮጵያ ታሸንፋለች።

ምንጭ:- ክቡር ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሀር

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *