አጠቃላይ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በድሬዳዋ

የብልጽግና ፓርቲ አጠቃላይ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በድሬዳዋ መካሄድ ተጀመረ።”አዲስ ፖለቲካዊ እይታ-አዲስ ሀገራዊ እመርታ” በሚል መሪ ቃል ለድሬዳዋ አስተዳደር አጠቃላይ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠናው የፓርቲው አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ከድር ጆሀር እና የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በድምቀት ተጀምሯል።የአስተዳደሩ አጠቃላይ አመራሮች ሥልጠናውን እንዲወስዱ በማድረግ የፓርቲውን የመሪነት ሚናና የመፈጸምና የማስፈፀም አቅም በማሳደግ የህዝቡ ተጠቃሚነት ማረጋገጥን አላማ ያደረገ ነው፡፡ ከ370 በላይ በአስተዳደሩ የሚገኙ የሴክተሮች፣ የከተማ ቀበሌዎችና ገጠር ክላስተሮች እንዲሁም የፌደራል ተቋማት አመራሮች በ10 ቡድኖች ለ5 ተከታታይ ቀናት በሚሰጠው ይህ ሀገራዊ ስልጠና ”አዲስ ፖለቲካዊ እይታ-አዲስ ሀገራዊ እመርታ” እና ሌሎች የአቅም መገንቢያ ሥልጠና ርዕሰ ጉዳዮች በመርሃግብራቸው መሰረት በአስተዳደሩ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው እንዲሁም የጋራ ግንዛቤና መግባባት እንደሚፈጠርባቸው ይጠበቃል።በትላንትናው እለት ስልጠናው በጥብቅ ድስፕሊን መመራት እንዳለበት ለሰልጣኞች ኦረነቴሽን እንደተሰጠ ይታወቃል።በቀጣይም ስልጠናው እስከታችኛው አመራርና አባላት ተጠናከሮ የሚቀጥል ይሆናል።ሀገርን/ ድሬዳዋን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅስለ ድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን የማህበራዊ ትስስር ገፆች በመከተል አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ❗️

ድረገጽ [ Website]www.diredawaprosperity.org

ፌስቡክ [ Facebook ]Prosperity Party – DireDawa

ቴሌግራም [ Telegram]https://t.me/ddppofficial2012

ትዊተር [ Tweeter]twitter.com/direprosperity

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *