በድሬዳዋ የሚከበረው የ16ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን አከባበር ዝግጅት በፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ዛሃራ ሁመድ ተጎበኘ።

#Dire_PP_Press🇪🇹 ህዳር 21/2014 ዓ.ምበድሬዳዋ የሚከበረው የ16ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን አከባበር ዝግጅት በፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ዛሃራ ሁመድ ተጎበኘ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ዛሃራ ሁመድ እና የ16ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን አከባበር አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በድሬዳዋ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን አከባበር ዝግጅት በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተዞዙረው ጎብኝተዋል። ህዳር 29 ቀን ለ16ኛ ጊዜ በድሬዳዋ አስተዳደር አዘጋጅነት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል የዝግጅት ሁኔታ የሚገኝበትን ደረጃ ለመመልከት ድሬዳዋ ሲደርሱ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ/ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር ፣ የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ የተከበሩ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እና ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በድሬዳዋ አለማቀፍ ኤርፖርት በመገኘት ደማቅ አቀባበል አድርጎውላቸዋል።በከሰአት ውሏቸውም የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡርና ባዕሉ የሚከበርበትን ሚሊኒዪም ፖርክ እና አዲሱ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተገኝተው የዝግጅቱን ሁኔታ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.