ለድሬደዋ ነዋሪዎችና ለመላ የኢትዮጵያ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ። እንኳን ለ1442ኛው የኢድ አልፊጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያልኩኝ በዓሉን ስታከብሩ እርስ በእርስ በመተጋገዝ፤ ጥላቻን በማስወገድ፣ ወንድማዊነትን በማጠናከርና ለአለም የሀይማኖቶች መቻቻል ተምሳሌት በመሆን እንድንቀጥል እያልኩ እንዲሁም ከኮቪድ-19 ራሳችንንና ወገኖቻችንን በመጠበቅ እንድናከብር መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።
እኛ የድሬዳዋ ነዋሪዎች እርስ በእርሳችን በመዋደድና በመተሳሰብ ለአገራችን ኢትዮጵያ እና ለከተማችን ድሬደዋ ፈጣሪ ሰላም እንዲያበዛላት እያልኩ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የብልፅግና እንዲሆንልን ለማለት እወዳለሁ።
በመጨረሻም ከፊታችን ያለው አገራዊ ምርጫ ጥቂት ቀናት በቀሩት የመራጮች ምዝገባ ጊዜ እስካሁን ያልተመዘገባችሁ ቶሎ በመመዝገብ የመራጭነት ካርድ በመውሰድ በድምፅ መስጫውም እለት ብልፅግናን እንድትመርጡ ስል መልእክቴን ለማስተላለፍ እወዳለሁ። መልካም በዓል !! “ኢድ ሙባረክ!”
![]()
