ከሁሉ አስቀድሜ በውቧ፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የአብሮነትና የመቻቻል ምሳሌ እና ማሳያ በሆነችው የበረሀዋ ንግስት ከተማችን ድሬደዋ አዘጋጅነት ለሚከበረው 16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ለማለት እወዳለሁ።

ከሁሉ አስቀድሜ በውቧ፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የአብሮነትና የመቻቻል ምሳሌ እና ማሳያ በሆነችው የበረሀዋ ንግስት ከተማችን ድሬደዋ አዘጋጅነት ለሚከበረው 16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ለማለት እወዳለሁ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች፤ የተለያዩ ሀይማኖት ተከታዮች ተዋደውና ተፋቅረው በአንድነት የሚኖሩባት፤ ብዝሀነት ጌጥና ድምቀቷ የሆነ፤ ለዘመናት በህዝቦቿ የጋራ ፍላጎት ጥረትና አንድነት የተገነባች፤ ከፍጥረቷ ጀምሮ ነፃነትና ክብሯን ጠብቃ የኖረች፤ በዚህም የአፍሪካና የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የነፃነት ምልክት መሆን የቻለች የጀግኖች ሀገር ናት::

ዛሬም ይሄው ክብርና ነፃነቷ ተጠብቆ እንድትኖርና ለትውልድ እንድትሸጋገር፤ ብርቱና ጀግና ልጆቿ ከውስጥም ከውጪም እንደ ሀገር የገጠመንን የህልውና አደጋና ጦርነት ለመመከትና በድል ለመደምደም፤ በአንድነት ህይወት ሰጥተውና ዋጋ ከፍለው ጠላቶቻችን ዳግሞ ላይነሱ እየቀበርናቸው የምንገኝ ሲሆን፤ ይህ ታሪካዊ ድል እየተመዘገበ ባለበት ግዜና ወቅት፤ 16ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአል በትንሿ ኢትዮጵያ ድሬዳዋ መከበሩ ልዩ አድርጎታል።

በመሆኑም መላው የአስተዳደራችን ነዋሪዎች፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ የልማት ድርጅቶች፣ ባለሀብቶች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሰራተኞች፣ የፀጥታ አካላት፣ በህልውና ዘመቻው ወደ ግንባር ከመዝመት ጀምሮ ስንቅ በማዘጋጀት የተለያየዩ ድጋፎችን በማድረግ፤ ለእናት ሀገር ፈጣን ምላሽ እንደሰጣችሁት ሁሉ፤ በአስተዳደራችን አስተናጋጅነት የሚከበረው 16ኛው የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል በፍፁም ሰላማዊነትና ድምቀት እንዲጠናቀቅ የበኩላችሁን እንድትወጡ ጥሬዬን አቀርባለሁ::

“ወንድማማችነት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት”
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘለአለም ትኑር!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *