“ከበዓሉ ማግስት ጀምሮ በአስተዳደራችን የጀመርነውን የልማት ጉዞ አጠናክረን እንቀጥላለን።” የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር

“ከበዓሉ ማግስት ጀምሮ በአስተዳደራችን የጀመርነውን የልማት ጉዞ አጠናክረን እንቀጥላለን።” የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያስተላለፉት መልዕክት።
===========================

በአስተዳደራችን የሚከበረው 16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል፤ መላው የድሬዳዋ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን፤ የአገራችንን በርካታ ውብ ዕሴቶች በአግባቡ እንድናውቅ፤ በወንድማማችነት መንፈስ ኢትዮጵያዊ ህብረታችንን ይበልጥ እንድናጎለብት፤ እንዲሁም… የእኛ የድሬዳዋውያን መገለጫ የሆነውን፤ በፍቅር እንግዳ የመቀበል መልካም ዕሴታችንን ይበልጥ እንድናጠናክር መልካም አጋጣሚ ይፈጥርልናል።

በትውልዶች ታሪክ የማይረሳ አስነዋሪ ድርጊት የፈፀመው አሸባሪው የህወሓት አረመኔ ቡድን፤ በኢትዮጵያውያን ብርቱ ክንድ ግብዓተ መሬቱ እየተፈፀመ በሚገኝበትና፤ መላው ኢትዮጵያዊያን በችግር ጊዜ በአንድነት የምንቆም ጽኑ ህዝቦች መሆናችንን፤ ለአለም በተግባር እያሳየን በምንገኝበት በዚህ ወቅት በዓሉ መከበሩ ደግሞ እጅግ ልዩ ያደርገዋል።

የፀጥታ አካላት፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና ግለሰቦች፤ እንዲሁም የንግዱ ማህበረሰብ፤ በአጠቃላይ መላው የድሬዳዋ ነዋሪዎች ለበዓሉ ስኬት የድርሻችሁን ጠጠር በመጣል ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪ እያቀረብኩ፤ በአስተዳደራችን ከዚህ ቀደም በሌብነት ሂደት ተከናውነው ህጋዊ የመሠሉ፤ በርካታ ህገ-ወጥ ድርጊቶችና ብልሹ አሰራሮችን በማፅዳት፤ የጀመርነውን አስተዳደራዊ የልማትና የዴሞክራሲ ጉዞ፤ ከበዓሉ ማግስት ጀምሮ አጠናክረን እንደምንቀጥል አረጋግጥላችኋለው።

#ወንድማማችነት ለሕብረ-ብሔራዊ #አንድነት

ክቡር አቶ ከድር ጁሀር
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ

Leave a Reply

Your email address will not be published.