የመደመር ትውልድ ምንዳ…..

የመደመር ትውልድ ምንዳ…..

ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ሁለንተናዊ ለውጥን ማሳካት እንደሚቻል ፓርቲያችን ያምናል። ለዚህም የሀገራችን መጠሪያ እስከመሆን የደረሰውን የድህነትን ታሪክ በመቀየር ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ለማድረግ ተግቶ በመስራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ አዲስ ምዕራፍ በመሸጋገር ላይ ይገኛል።

ብልጽግና በዘረጋው ዘመንን የተረዳ የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ስርዓት ትክክለኛነት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በማንገብ ከህዝብ ጋር ተናባቢ በሆነ ተግባር ዕምርታዊ ለውጦችን አስመዝግቧል። ይህ ትውልድ ታሪክ ከመዘከር በተጨማሪ ምርታማነትን እያሳደገ ፤ የምግብ ዋስትናን እያረጋገጠ ሀገራዊ ብልፅግናን እውነት በማብሰር የራሱን አሻራ አሳርፎ ታሪክ እየሰራ ይገኛል።

ከተረጅነትና ጠባቂነት ዕሳቤ በመላቀቅ ለሁለንተናዊ ከፍታ መትጋት ወሳኝ ነው። ብልጽግና ባስቀመጠው የኢኮኖሚ መርሃግብር መሰረት ለቀጣይ ትውልድ መሰረት የሚሆን የስራ ባህልን በመገንባት በእራስ አቅምና ጥረት ሰርቶ መበልጸግ እንደሚቻል ማስመስከር ተችሏል። በመሆኑም ሀገራዊ ክብርን በሚመጥን መልኩ ትውልድ ተሻጋሪ ምንዳና አሻራን ለማኖር ትሩፋቶችን እያሰፉና እያዘመኑ ማስቀጠል ይጠበቃል።

ከዚህ የመደመር ትውልድ የሚጠበቀው ባለፈ ታሪክ ከመቆዘም ወጥቶ በተጀመረ የብልጽግና መደመር መንገድ ከምክንያት በላይ ሆኖ መስራት ብቻ ነው። እንደሚታወቀው ሀገራችን በተፈጥሮ ሀብቷ የበለፀገች ለአፍሪካዊያን ሁሉ ኩራት ሊሆን የሚያስችል ዕምቅ ሀብት ባለቤት ነች። ይህን ሀብት በአግባቡ ማልማትና መጠቀም ከተቻለ ታላላቅ ሀገራት ከተሰለፉበት ከፍታ በመድረስ ተምሳሌታዊ ብልጽግናን የማናረጋግጥበት ምንም ምክንያት አይኖርም።

የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ አካባቢ ተኮር ግጭቶች እና የመሳሰሉ አሉታዊ ሁኔታዎችን በመከላከል በህብር ደምቀን በአንድነት የምንበለፅግበት መንገድ በእጃችን ነው፡፡ ከተናጠል እውነት ይልቅ የወል ዕውነቶቻችንን በማጽናት ታሪካችንን በሚመጥን መልኩ ኢትዮጵያችንን በብልጽግና እና በክብር በአንድነት የተፈጥሮ ሀብቷን በአግባቡ በመጠቀምና በማስተዳደር ሁለንተናዊ ከፍታዋን በማብሰር በዓለም አደባባይ ቀና ብለን መራመድ የምንችልበት ሁኔታን መፍጠር ይጠበቅብናል።

ባለብዙ ፀጋዋ ኢትዮጵያ የእራሷን ችግር በልጆቿ የተባበረ ክንድ በመፍታት በዓለም አደባባይ ቀና ብላ የምትታይበት ጊዜው አሁን ነው። ይህ ትውልድ ዘመንን የዋጀ የመደመር ዕሳቤን አንግቦ ለሁለንተናዊ ብልጽግናዊ ተምሳሌትነት በፍጹም ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለጋራ ለውጥ በጋራ እየተጋ ይገኛል። ኢትዮጵያ በልጽጋ ልጆቿም ከስብራታቸው አገግመው ቀና ብለው የሚራመዱበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፤ ዛሬን ከትናንት አስተሳስረን ነገን የምነገነባ የመደመር ትውልዶች ነን።

ሳንጠቀምበት በቀረነውና የባከነ ጊዜና ሀብት ቁጭትን በመፍጠር በይቻላል መንፈስ የስራ ባህልን መለወጥና መትጋት ተገቢ ነው። ይህንን የቁጭትና የትጋት ግለታችንን ማስቀጠል ከቻልን የሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞአችን ስኬትም ሩቅ አይደለም። እምቅ አቅሞቻችንን ወደ ውጤት ለመቀየርም የምንችልበት ምቹ ሁኔታ መኖሩን በተግባር ያሳካናቸው ውጤቶች ያሳያሉ።

በመሆኑም ፀጋዎችን በአግባቡ የመጠቀም ልምድ በማስፉት ምርታማነትን በመጨመር የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ በዘለለ ሀገራዊ ክብርን መመለስ ይቻላል። የዚህ ትውልድ አደራ የሚሆን በቁጭት በስራ ተግቶ ህብረብሔራዊ አንድነቱን በመጠበቅ መጭው ትውልድ በዓለም አደባባይ በኩራት ኢትዮጵያዊነቱን የሚዘክርበት አውድ መገንባት ብቻ ነው። ለቀጣይ ትውልድ ዕዳን ሳይሆን ምንዳን፣ ከልዩነት ይልቅ ህብረብሔራዊ አንድነትን፣ ከድህነት በላይ ባለፀጋነትን በማውረስ ሁለንተናዊ ብልጽግናን እናበሳራለን።

#DIREPROSPERITY

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *