“የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የ2016 የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሀግብር ተካሄደ።

“የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የ2016 የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሀግብር ተካሄደ።

ሐምሌ 01 ቀን 2016 ዓ.ም

#DIREPROSPERITY PARTY🇪🇹 DIRE

ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት መንግስት ስትራቴጂዎችን ነድፎ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የአረንጓዴ አሻራ መሆኑን በመርሀግብሩ መክፈቻ ንግግራቸው ላይ የገለፁት የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ ናቸው።

ባለፉት ተመሳሳይ መርሀግብሮች 5.7 ሚሊየን በላይ ችግኞች በአስተዳደሩ ህዝብ ተሳትፎ መትከልና ማፅደቅ ተችሏልም ሲሉ አቶ ኑረዲን አብደላ አክለው ገልፀዋል።

የተራቆተ የደን ሀብታችንን መልሶ እንዲያገግምና የደን ሽፋናችን እንዲሻሻል አስተዳደሩ ለአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ትልቅ ትኩረት በመስጠት ለዘንድሮው ችግኝ ተከላ መርሀግብር በ20 ችግኝ ጣቢያዎች 3 ሚሊየን የነዋሪውን የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጡ ችግኞችን በማፍላት ያዘጋጀና በ1200 ሄክታር መሬት ላይ በህዝብ ተሳትፎ ለመትከልና ለማፅደቅ መሰራቱም ተገልጿል።

በመርሀግብሩ መተግበር የድርቅ ተጋላጭነት እንዲቀንስ፣ የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ፣ የጎርፍ አደጋ እንዲቀንስ እንዲሁም በስራ እድል ፈጠራ ወጣቱ በተለያዩ የግብርና ስራዎች ተሰማርቶ ተጠቃሚ እንዲሆን አስችሏል።

በኢፌዴሪ ጠ/ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ በ2011 ዓ.ም በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በሀገር ደረጃ እስካሁን 32.5 ቢሊየን ችግኞች መተከሉንና በዘንድሮው ዓመት ደግሞ 7.5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱንና በዚህም የአገራችንን የደን ሽፋን ወደ ሰላሳ በመቶ ለማድረስ በቁርጠኝነት በመሰራት ላይ መሆኑን የገለፁት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ናቸው።

የድሬዳዋ አስተዳደር ለጎረቤት አገር ጅቡቲ ባለፈው ዓመት ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ችግኞችን የለገሰ መሆኑንና ዘንድሮም በተመሳሳይ ችግኞች እንደሚሰጡ በዚህም የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብራችን የሀገራችንን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር አስተዋፅኦ አበርክቷል በማለት ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ተናግረዋል።

የአስተዳደሩ ካቢኔ አባላት፣ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊና አመራሮች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች የተገኙበት የዛሬው የ2016 የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሀግብር በድሬዳዋ አስተዳደር በዋሂል ወረዳ ሐርላ ገጠር ቀበሌ ተከናውኗል።

#DIREPROSPERITY

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *