የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ በትግራይ ክልል በሰው ሠራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ለተጎዱ ሴቶች የሚውል የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ በትግራይ ክልል በሰው ሠራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ለተጎዱ ሴቶች የሚውል የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዛሃራ ሁመድ ብልፅግና ፓርቲ የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ ነው ብለዋል።

ሊጉ ሀገር የሚገጥማትን ፈተናዎች በጽናት እና በድል ለመወጣት በሚደረገው እንቅስቃሴ ግንባር ቀደም ሆኖ እየሠራ መቆየቱን ገልፀዋል። የአገራችን ሰላም ለማረጋገጥ በሚካሄደው ጥረትም ሊጉ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ አደጋ በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመታደግ በርካታ ንቅናቄዎችን ሲያደርግ መቆየቱንም አንስተዋል።

በዚህም መሰረት “ሁለት መቶ ለእናቴ” በሚል መሪ ቃል በተደረገ ሀገራዊ ንቅናቄ ሊጉ ሴቶችን በማስተባበር እና ከኅብረተሰቡ ሃብት በማሰባሰብ ለተጎዱ ቤተሰቦች ሲደርስ መቆየቱን ጠቅሰዋል።

በዚህ አገራዊ ንቅናቄ ለትግራይ ክልል ለሚገኙ በሰው ሰራሽና ተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለተደሰባቸው ሴቶች ድጋፍ የሚውል ሁለት ሚሊየን ሰባት መቶ ሰላሳ አንድ ሺ ሰባት መቶ ስምንት ብር ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

ድጋፍን የተረከቡት የትግራይ ክልል ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ፍሬወይኒ ገ/እግዚአብሄር ለተደረገዉ ድጋፍ ምሰጋናቸዉን አቅርበዉ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ።

በርክክብ መርሀ ግብሩ ላይ የሊጉ ም/ፕሬዚዳንቶች ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን እና ወ/ሮ መስከረም አበበ እንዲሁም የትግራይ ክልል ሴቶች አደረጃጀት ተገኝተዋል።

#DIREPROSPERITY

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *