#DireProsperity🇪🇹 ታህሳስ 5/2014የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት፤ 3ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አመት 7ኛ አስቸኳይ ጉባኤ፤ የተለያዩ አዋጆችና ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቋል። ምክር ቤቱ በጉባኤው የድሬዳዋ አስተዳደር አስፈፃሚና ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት አካላትን እንደገና ለማቋቋምና፣ ተግባርና ኃላፊነታቸውን ለመወሰን የወጣ አዋጅ፤ የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን ማፅደቂያ ረቂቅ አዋጅ፤ እንዲሁም የከተማ ፕላን ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ በመወያየት ያፀደቀ ሲሆን፤ ጉባኤው የሚከተሉትን ዕጩዎች ማለትም:

-1- አቶ ሻኪር አህመድ፣

2- አቶ ደረጀ ፀጋዬ እና

3- አቶ ገዛኸኝ ታዲዮስ፣ በአስተዳደሩ ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ እንዲሆኑ ተሹመዋል።

1- ደቻስ ኡስማኤል፣

2- አብዱልማሊክ መሀመድ፣

3- ሮቤል አለማየሁ፣

4- ፈቲያ በያን፣

5- አብዱልፈታህ ጣሂር እና

6- ባይሳ ጅሩ የአስተዳደሩ ይግባኝ ሰሚ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ሆነው እንዲሾሙ ም/ቤቱ አፅድቋል። ከዚህ በተጨማሪ 28 የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት፤ በ7 የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ውስጥ አባል እንዲሆኑ ሹመታቸው ፀድቆ፤ ሁሉም ተሿሚዎች በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.