የክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ብራ ፋውንዴሽን ምስረታ፥ በአዲስ አበባ ይፋ ሆኗል

#ዜና | የክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ብራ ፋውንዴሽን ምስረታ፥ በአዲስ አበባ ይፋ ሆኗል።

የፋውንዴሽኑ መመስረት አርቲስቱ በህይወት ሳለ የጀመራቸውን ሥራዎች ማስቀጠል እና ለትውልድ ማስተላለፍን ዓላማው ያደረገ ነው ተብሏል።

በተለይም አርቲስት አሊ ብራ በህይወት እያለ በትምህርት እና በማህበራዊ መስኮች የጀመራቸውን ሥራዎች ከግብ ማድረስ ዋነኛው ትኩረት መሆኑም በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

የክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ብራ ፋውንዴሽን ምስረታ ይፋ በተደረገበት መርሀግብር ላይ የአርቲስቱ ባለቤት ወ/ሮ ኢሊሊ ብራ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የብልፅግና ፖርቲ ድሬዳዋ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍን ጨምሮ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች፥ የፌዴራል እና የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ድምፃውያን እና የአርቲስቱ ወዳጆች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

መሐመድ ዩሱፍ

ምስል – ምንተስኖት ደረጀ

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *