የድሬደዋ ወጣቶች ፌደሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ እና የፌደሬሽን ስራ አስፈፃሚ ምርጫ በዛሬው ቀን ተከናወነ።

#DIREPROSPERITY🇪🇹 ሀምሌ 23/2014

የድሬደዋ ወጣቶች ፌደሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ እና የፌደሬሽን ስራ አስፈፃሚ ምርጫ በዛሬው ቀን ተከናወነ።

በድሬዳዋ አስተዳደር በዛሬው እለት በተለያዩ መዋቅር ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን በፌደሬሽን በማቀፍና የቀድሞ የወጣት ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚዎች ለተተኪው ያስረከቡ ሲሆን የተጓደሉትን ደግሞ እንደ አዲስ በማስመረጥ የፌደሬሽን ስራ አስፈፃሚና ኦዲት ቁጥጥር ምርጫ ተከናውኗል።

የድሬዳዋ ወጣት ፌዴሬሽን ጉባኤ ስራ አስፈጻሚዎችና ኦዲት ቁጥጥር ህብረብሔራዊነቱን የጠበቀ አደረጃጀት መሰረት ተሰይሟል። በዚሁ መሰረት

➙የድሬዳዋ ወጣት ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚዎች:-

1. ሀሚድ አብደላ :- የድ.ዳ.ወ.ፌ.ፕሬዚዳንት

2. አሪፍ አደን :- የድ.ዳ.ወ.ፌ.ቀ.ም.ፕሬዚዳንት

3. አማረ ጥላሁን :- የድ.ዳ.ወ.ፌ.ተ.ም.ፕሬዚዳንት

4. ኢ/ር ሰምሩ ፍቅሬ :- የድ.ዳ.ወ.ፌ. ዋና ጸሐፊ (የጽ/ቤት ኃላፊ)

5. ሙስጠፋ ኑሬ :- የድ.ዳ.ወ.ፌ. ቀ.ም. ጸሐፊ (የጽ/ቤት ም/ ኃላፊ)

6. ኢ/ር ነቢል አብዱልከሪም :- የድ.ዳ.ወ.ፌ.ሂሳብ ሹም

7. ፈልመታ መሐመድ :- የድ.ዳ.ወ.ፌ.ስልጠና ዘርፍ ሀላፊ

8. ጎሳዬ አዳነ :- የድ.ዳ.ወ.ፌ.ትምህርት ዘርፍ ኃላፊ

9. አብዱረሺድ ሲራጅ:- የድ.ዳ.ወ.ፌ.የኢኮኖሚ ዘርፍ ኃላፊ

10. መሐመድ አብዱልቃድር :- የድ.ዳ.ወ.ፌ.የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ

11. ሮባ ኡስማኢል :- የድ.ዳ.ወ.ፌ.ገንዘብ ያዥ

➙ኦዲት ቁጥጥር ኮሚቴዎች

1. ኦሮሚያ መሐመድ

2. ዮርዳኖስ ግርማ

3. ፋሲካ አፈወርቅ

በማድረግ በአብላጫው ድምጽ ተመርጠዋል።

በመርሃግብሩ መሰረት ለነባር ስራ አስፈጻሚዎች የምስጋና እና የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷቸዋል።

የድሬዳዋ ወጣቶች ፈዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲካሄድ ጉልህ አስተዋጽኦ ያደረጉና ከወትሮ ባልተለመደ መልኩ የስልጣን ርክክብ ላደረጉ ለቀድሞ የድ.ዳ.ወ.ፌ.ፕሬዚዳንት እስክንድር አህመድ እና ም/ፕሬዚዳንት ባንታለም ግርማ ጨምሮ ለአገልግሎት ጊዜያቸውና ጠቅላላ ጉባኤ እንዲካሄድ ላደረጉት ቀና ትብብር በወጣቶች ስፖርት ኮሚሽን የወጣቶች የስራ ሂደት ሀላፊ በአቶ መሐዲ ሰመር በኩል የምስጋና እና የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

ስላገለገላችሁን እናመሰግናችኋለን 🙏

መልካም የስራ ጊዜ

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *