የድሬዳዋ አስተዳደር መሰረታዊ ድርጅቶች የ2016 ማጠቃለያ ኮንፈረንስ አካሄዱ

የድሬዳዋ አስተዳደር መሰረታዊ ድርጅቶች የ2016 ማጠቃለያ ኮንፈረንስ አካሄዱ።

ሰኔ 29 ቀን 2016

#DIREPROSPERITY PARTY🇪🇹 DIRE DAWA በድሬዳዋ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ መሰረታዊ ድርጅቶች የ2016 ማጠቃለያ ኮንፈረንስ አካሂደዋል።

የጠንካራ ፓርቲ ምልክት ህዋሳት በአግባቡ መወያየታቸው፤ አመራሩና አባሉ በአስተሳሰብና በአመለካከት ተመሳሳይ መሆን ሲችልና ከመሰረታዊ ድርጅት አባላት ወይም ህዋሳት የሚፈልገው ሁለት ነገር ግንባር ቀደም መሆንና ብልሹ አሠራርን መታገል እንደሆነ ተጠቁሟል።

የፖለቲካ ሥራ አመለካከት ላይ የሚሠራና በአንድ ጊዜ ተሠርቶ የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ የ2016 አፈፃፀም ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና ደካማ ጎኖችን ደግሞ በማስተካከል ፓርቲያችን በፕሮግራሙ በሁሉም ዘርፍ ያስቀመጣቸውን ሥራዎች ለማሳካት መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።

በ2016 በርካታ እንደ ፓርቲም ሆነ እንደ መንግስት በመቀናጀት ለውጤታማነቱም የአባላቱ መልካም ስነ-ምግባር፣ ፅናትና ጥንካሬ የመላው ሠራተኛ ተነሳሽነት ያመጣው ውጤት በመሆኑ የፓርቲ አመራሮችና ከሴክተር መ/ቤት እስከ ወረዳና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች ለፓርቲ ስራ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግም ተመላክቷል።

በዚህ የአመቱ ማጠቃለያ ኮንፈረንስ ላይ የመሰረታዊ ድርጅቶች የ2016 የስራ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2017 የስራ እቅድ የቀረበ ሲሆን በቀረበው እቅድና ሪፖርት ላይም ከአባላቱ ሀሳብ ቀርበው በመወያየት ፀድቋል።

በተጨማሪም የመሰረታዊ ድርጅት የኦዲት እንስፔክሽን ሪፖርትና እቅድ ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የአሰራር ክፍተቶችን በማረም ሂደት ሁሉም እንዲረባረብ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

መሰረታዊ ድርጅቶቹ ባካሄዱት ኮንፈረንስ እጩ አባላት ወደ ሙሉ አባልነት እንዲሸጋገሩ በማድረግ ኮንፈረንሶቹን አጠናቀዋል።

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *