የብልፅግና ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዋና ዋና ነጥቦች:-

ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በፉክክር እና በትብብር መካከል ሚዛን በመጠበቅ፣ ተቃርኖዎችን በማስታረቅ የሚጓዝ መሆን እንዳለበት ያምናል።ሃገራዊ ክብርን ያስቀደመ፣ ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ፣ ጎረቤት አገራትን ያስቀደመ የውጭ ግንኙነት፣ ቀጣናዊ ትብብርና የኢኮኖሚ ውህደት የሚሉት ብልፅግና ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራባቸው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ አንኳር ጉዳዮች ናቸው።የፓርቲያችን የውጭ ግንኙነት እሳቤ የሚመጨው ጥቅምን ከማሳደድ ሳይሆን ግንኙነትን እና መልካም ትብብርን ከማስቀደም ነው። በዚህም ረገድ ብልፅግና ግንኙነትን ማደስ ብሄራዊ ጥቅምን ለማስከበር አዎንታዊ ሚና እንዳለው ያምናል።ብሄራዊ ጥቅም በአንድ ወገን ሊበየን የማይችል እና ወጥና የማይለወጥ እንዳልሆነ ከግንዛቤ በማስገባት የአገሪቷን እሴቶች ተከትሎ በትብብርና በንግግር ጥቅምን ማስከበር እንደሚገባ ብልፅግና ያምናል።የውጭ ግንኙነታችን ሌላው አንኳር ነጥብ ብሄራዊ ክብርን በማስጠበቅ አገራችን ሉዓላዊነቷን አረጋግጣ፣ ታፍራና ተከብራ የምትኖር ጠንካራ አገርን በማረጋገጥ ረገድ ብልፅግና ተግቶ ይሰራል።የለውጡ አመራር ወደ ሃላፊነት ከመጣ በኋላ በተለያዩ የአረብ አገራት የሚገኙ ዜጎችን ከነበሩበት ፈታኝ ሁኔታ በማላቀቅ ወደ ውድ አገራቸው እንዲመለሱ የማድረግ ተግባር ተከናውኗል። የዜጎች ክብር የብሄራዊ ክብራችን አይነተኛ መገለጫ እንደሆነም ፓርቲያችን ያምናል። ለዚህም ጠንክሮ ይሰራል።ፓርቲያችን ከጎረቤት አገራት ጋር የሚኖር ግንኙነት በመነጋገርና በመተባበር ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ሲሰራ ቆይቷል፤ ወደ ፊትም አጠንክሮ ይቀጥልበታል። የኢትዮጵያና የጎረቤቶቿ እጣ ፈንታ የተሳሰረ በመሆኑና የጋራ ጥቅማችንን መሰረት ያደረገ መተጋገዝና ትብብር መመስረት እንደሚገባ ብልፅግና ያምናል።በቀጠናው ከሚገኙ አገራት ጋር የሚፈጠር ግንኙነት በፍፁማዊ የጋራ ጥቅም ላይ ተመስረቶ ቀስ በቀስ እያደገ ሄዶ ወደ ጠንካራ ምጣኔ ሃብታዊ ጥምረት እንዲያድግ ፓርቲያችን አስፈላጊውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ያደርጋል።ፓርቲያችን የጋለ የአገር ፍቅር ስሜት ያላቸው፣ በትምህርትና ስልጠና የካበተ ልምድ ያላቸውና በማህበረሰቡ ቅቡልነትና እውቅና ያላቸው ግለሰቦችን በተለያዩ አገራት በአምባሳደርነት በመመደብ የአገሪቷ ዲፕሎማሲ እንዲጠናከር ይሰራል። በዲፕሎማሲው ጎራ ብቃት ያላቸው ዲፕሎማቶችን ለማፍራት የሚያስችሉ የምርምርና የስልጠና ልህቀት ማዕከላትን በማስፋፋት ኢትዮጵያ ጠንካራ የውጭ ግንኙነት እንዲኖራት ፓርቲያችን ይተጋል።የተጠናከረ የውጭ አገራት መስተጋብርን በመፍጠር ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ወደ አገራችን እንዲመጣ ዲፕሎማሲያችን አብይ ሚናውን እንዲወጣ ብልፅግና ያላሰለሰ ስራ ይሰራል።#ብልጽግናምርጫዬነው!#ነገዬበእጄላይነው!#Prosperityismychoice#Ichoosemyfuture

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *