በአስተዳደሩ ከሚገኙ ምሁራን፣ ባለሀብቶችና የንግዱ ማህበረሰብ ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

#DireProsperity🇪🇹 ታህሳስ 6/2014በአስተዳደሩ ከሚገኙ ምሁራን፣ ባለሀብቶችና የንግዱ ማህበረሰብ ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ። በውይይቱ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ የመንግስትና የግል ኮሌጆች፣ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ምሁራንና መምህራን እንዲሁም ባለሀብቶችና የንግዱ ማህበረሰብ ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሱ የውስጥና የውጭ ጠላቶችን በተጠናከረ አንድነትና ብስለት ጦርነቱን በመምራት የመጀመሪያው ምዕራፍ በድል ማጠናቀቅ መቻሉንና፤ በቀጣይ የተፈናቀሉትን በማቋቋም ወደ ሰላም መምጣትና የኢትዮጵያ ልማት ማፋጠን እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቷል። በብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በተመራው መድረክ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ በወቅቱ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ፤ እንዲሁም ትኩረት የሚሹ አገራዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በመለየት ቀጣይ የጉዞ አቅጣጫ ተቀምጧል።

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *