ታህሳስ 7/2014በድሬዳዋ አስተዳደር ከሚገኙ የሀይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ አባገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ተካሂዷል

#DireProsperity🇪🇹 ታህሳስ 7/2014በድሬዳዋ አስተዳደር ከሚገኙ የሀይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ አባገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ተካሂዷል። በመድረኩ ከወቅታዊው ሁኔታ አንፃር አካታች አገራዊ ምክክር የማድረግ አስፈላጊነት፤ እና የሀይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ሊኖራቸው በሚገባው ሚና ዙሪያ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። በህልውና ዘመቻው በሁሉም መስክ በተደረገው ድጋፍ የሀይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች የነበራቸው ድርሻ ከፍተኛ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፤ በቀጣይ የመልሶ ማቋቋም ተግባር ተሳትፏቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ከመድረኩ ጥሪ ቀርቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.