“3ኛውን ዙር ውኃ ሙሌት በታሰበው ጊዜ ማጠናቀቅ ስለቻልን የዓባይ ልጆች ሁሉ እንኳን ደስ ያለን” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

“3ኛውን ዙር ውኃ ሙሌት በታሰበው ጊዜ ማጠናቀቅ ስለቻልን የዓባይ ልጆች ሁሉ እንኳን ደስ ያለን” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

*********

“የሕዳሴ ግድብ 3ኛው ዙር ውኃ ሙሌት በስኬት ተጠናቅቋል፡፡

ዓባይ ላይ ግድብ ለመገንባት ስንነሳ ወንዙን የራሳችን ብቻ የማድረግ ፍላጎት አድሮብን እንዳልሆነ ከመጀመሪያውም ስንናገር ነበር፡፡ እኛ ማግኘት የሚገባንን ጥቅም እናግኝ ስንል ልክ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ ሌሎቹ የዓባይ ሥጦታዎች – ሱዳንና ግብጽ ከወንዙ በየድርሻቸው እንደሚጠቀሙበት እያሰብን ጭምር ነው፡፡ እውነትን ይዘን ተነስተን፣ በገዛ ሐቃችን ገንብተን፣ በቃላችን መሠረት፣ ማንም ላይ ጉዳት ሳናደርስ እነሆ 3ኛውን ዙር ውኃ ሙሌት በታሰበው ጊዜ ማጠናቀቅ ስለቻልን የዓባይ ልጆች ሁሉ እንኳን ደስ ያለን!!

የዓባይ ወንዝ ለሺህ ዘመናት ሦስቱን ሀገራት አስተሳስሮ እንዳኖራቸው ሁሉ፥ በእሱ ላይ የተገነባው ግድብ ከሌሎች ጎረቤቶቻችንም ጋር በትብብር እንድንኖር ያስችለናል፡፡ ግድቡ ደለል የሚያስቀር በመሆኑ በጎርፍ ምክንያት በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የሚወድመውን ሀብትና የሚጠፋውን የሰው ሕይወት ቁጥር እንደሚቀንስ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ባለፈ ግድቡ የሚያመነጨውን ኤሌክትሪክ – በኃይል ምንጭነት፣ በውኃው አናት ላይ የሚነጠፈውን ውብ ገጽታ -በመዝናኛነት፣ በውኃው ጉያ የሚሰግሩትን አሳዎች – በምግብነት ከጎረቤቶቻችንና ከዓለም ጋር እንጋራዋለን፡፡”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *