#Dire_PP_Pres ህዳር 29/2014 ዓ.ም ወንድማማችነት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል 16ኛ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ሲምፖዚየም

#Dire_PP_Press🇪🇹 ህዳር 29/2014 ዓ.ም ወንድማማችነት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል 16ኛ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ሲምፖዚየም በድሬዳዋ በልዩ ሁኔታ ተካሄደ።በአስተዳደራችን አስተናጋጅነት የተካሄደው 16ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ሲምፖዚየም ላይ በቀረቡ 3 የጥናታዊ ጽሁፎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡በሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች በርካታ ሀሳቦች አንስተው በቂ ምላሽ የተሰጠባቸውና በቀጣይ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ተለይተዋል፡፡ መድረኩን የመሩት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር ህብረብሄራዊነታችን ማጌጫ እንጂ መጋጫ እንዳልሆነና ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ታግለው መብታቸውን ሊያስከብሩ ይገባል ያሉ ሲሆን ለሌሎች ሳይሆን ለውድ አገራችን እጣ ፋንታ ስንል የምንታገለውን አካል በትክክል አውቀን መታገል ያስፈልጋል ይህ ባይሆን ግን እንዳሁኑ ዋጋ ያስከፍለናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የእለቱ ክብር እንግዳ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ ሠላም የሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ በደንብ መያዝ የሚገባው ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ማንም አካል ወደ ውግያ የሚገባውን ለሰላም ፍለጋ ነው ብለዋል። በመጨረሻም በድሬደዋ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 16ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል በቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ 17ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንዲያዘጋጅ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ተመርጧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.