ህዳር 21/2014 ዓ.ም የተከበራችሁ የድሬዳዋ ነዋሪዎች:-

የተከበራችሁ የድሬዳዋ ነዋሪዎች:-ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት ከእኛ ይጠበቃልና፤ እኔም ከሌሎች ወንድሞቼ ጋር ወደ ትግሉ ሜዳ ለመዝመት ተዘጋጅቻለሁ። በግንባር ተገኝተን ያዘጋጀነውን ስንቅ እናቀብላለን፤ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ጀግናው ሠራዊታችንን በወኔ እናበረታታለን። የአስተዳደራችን የፀጥታ ኀይሎችና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችም፤ ከመቼውም ጊዜ በላይ የድሬዳዋን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ፤ የልማትና አስተዳደራዊ ሥራዎችን በሙሉ አቅማቸው ለማከናወን ተዘጋጅተዋል። መላው ነዋሪዎች አካባቢያችሁን በመጠበቅ፤ ሠራዊቱን በመደገፍና፤ ወደ ግንባር […]

ብልጽግና ፓርቲ ማጠቃለያ ኮንፈረንስ ተካሄደ

#Dire_PP_Press ህዳር 19/2014 ዓ.ም #Dire_PP_Press ህዳር 19/2014 ዓ.ም የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ማጠቃለያ ኮንፈረንስ ተካሄደ። በድሬዳዋ አስተዳደር በአይነቱ ልዩ እና የመጀመሪያው የሆነው የብልጽግና ፓርቲ ኮንፈረንስ በህሊና ጸሎት የተጀመረው የዝግጅት ምዕራፍ ማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል። በመክፈቻ ንግግር መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከውስጥና ከውጭ የጥፋት ሃይሎች ህልውናዋን የሚፈታተን አደጋ ገጥሟት አሸንፋ […]

የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ የማጠቃለያ የምርጫ ቅስቀሳ መርኀግብር በድምቀት ተካሄደ።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከየካቲት 8 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅቶች ነበሩ። ግንቦት 28 ይደረጋል በተባለው ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳው የሚያበቃው በግንቦት 23 ነበር። ሆኖም ምርጫው ወደ ሰኔ 14 መዛወሩን ተከትሎ የምርጫ ቅስቀሳውም አብሮ መራዘሙ ይታወሳል። የምርጫ ቅስቀሳው ከመጭው አርብ በፊት ተጠናቆ ምንም ቅስቀሳ ወደማይካሄድበት ወደ የጥሞና […]

ሀገራዊና ጂኦ-ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር በማድረግ፣ ከብልጽግና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተላለፈ መልእክት

የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ልጆች፣የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ክቡራትና ክቡራን፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትገኝበት ጂኦ ፖለቲካዊ ከባቢ ዛሬም እንደ ትናንቱ የዓለም ዓይን ማረፊያ ሆኖ ይገኛል። ከሜዲትራንያን ባሕር ቀጥሎ በዓለም ታሪክ ላይ በሚደረጉ የንግድና ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች የሚጠቀሰው ቀይ ባሕር ነው። በዚህ ቀጣና ላይ የበላይነት መያዝ በዓለም አቀፍ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ይታመናል። እናም ብዙ ሀገራት ከሌላ የዓለም ዳርቻ […]

ግድቡ ኢትዮጵያ ሃብቷን በራሷ አቅም አልምታ ችግሮቿን መፍታት እንደምትችል የምታሳይበት ነው … ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ

ግድቡ ኢትዮጵያ ሃብቷን በራሷ አቅም አልምታ ችግሮቿን መፍታት እንደምትችል የምታሳይበት ነው … ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ሃብቷን በራሷ አቅም አልምታ ችግሮቿን መፍታት እንደምትችል የምታሳይበት ፕሮጀክት ነው ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ገለጹ። ዶክተር ቢቂላ በኢትዮጵያ እየተገነቡ በሚገኙ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ዜጎች ንቁ ተሳትፎ እንድያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ […]

የትምህርቱ ዘርፍ ችግሮቻችን በብልጽግና ይፈታሉ

ከኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት ከፍተኛ ሀብት ሲመደብለት የቆየው የትምህርት ዘርፍ፤ ከፍተኛ የጥራትና የተደራሽነት ችግር የሚታይበት በመሆኑ ፓርቲያችን ብልጽግና ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ልዩ ትኩረት በመስጠት ችግሩን ለማቃለል ጥረት አድርጓል፡፡ እንደሚታወሰው፤ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ በየአምስት (ስድስት) ዓመታቱ ልዩነት ክለሳ ሊደረግበት የሚገባ ቢሆንም፤ ፖሊሲው ከ20 ዓመታት በላይ ሳይታይ ቆይቷል፡፡ ከብልጽግና በፊት በነበሩ 15 ዓመታት ትኩረት የተሰጠው የትምህርት ማስፋፋት ነበር፡፡ […]

ለወጣቱ ልዩ ትኩረት የሰጠው ብልጽግና!

ወጣትነት- በአካል የጠነከረ፣ በመንፈስ የቀደመ፣ ለውጤት የቸኮለ እምቅ አቅም ያለው ኃይል ነው። ይህን ኃይል በተደራጀና በተገቢ መንገድ ከተመራ ስኬትን ማጣጣም እንደሚቻል ብልጽግና ፓርቲ በጽኑ ያምናል። ወጣቶችን የስራዎቹ ሁሉ ማዕከል አድርጎ ያያቸዋል፤ ለጠንካራ አገር ግንባታ መሰረት መሆናቸውን ይቀበላል። በመሰረቱ ወጣቶች ለዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ ፈተናዎች እንዳሉባቸው ብልጽግና ይረዳል። ተምረው ስራ ማጣት፣ ስራ ቢቀጠሩም በቂ ገቢ ያለማግኘት፣ ለስራ […]

ብልጽግናና መልካም እሴቶች አይነጣጠሉም!!

ኢትዮጵያውያን በዘመናት ውስጥ እርስ በርስ ተሳስረዋል፤ በጠበቀ ማንነት ተጋምደዋል። በዓለም ዘንድ ታላቅ በሚያደርጋቸው እነርሱነታቸው ተሰናስነዋልም። የእነርሱ ጥብቅ መተሳሰር የመጣው በዘመናት ሂደት ነው። ለዚህ የተለያዩ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል። በዘመናት ውስጥ ደማቸውን ቀለም፣ አጥንታቸውን ብዕር አድርገው የጻፉትን መልካም ታሪክ ዋቢ ማድረግ እንደሚቻል ብልጽግና ፓርቲ ያምናል። በብልጽግና አተያይ ኢትዮጵያውያን ከውጭ የመጣን ጠላት ለመከላከል፣ ለማጥቃትና የጋራ ክብራቸው እንዳይገሰስ ለማድረግ […]

ብልጽግና ቃሉ ተግባር የሆነ ፓርቲ!

ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ያደሩ የቤት ስራዎቸ አሉ። እነዚህን ለይቶና በቅደም ተከተል አቅዶ የመተግበር አስፈላጊነት አጠያያቂ አይሆንም። ለዚህም ነው ፖለቲካው ሲታመም የተገራገጨውን ኢኮኖሚና ለዓመታት ሲንከባለል የመጣው ማህበራዊ ቀውስ በፍጥነት ታቅዶ መስመር ካልያዘ ለአገር አደገኛ መሆኑን የለውጥ ኃይሉ በመገንዘብ ጊዜ ሳይወስድ አፋጣኝ መፍትሄ የሰጠው። ስለሆነም የለውጥ ኃይሉ ሁሉንም ለመፍታት ማቀድ፣ ያቀዱትን ተግባራዊ ለማደረግ መንቀሳቀሱን ቀዳሚ ተግባሩ አደረገ። […]

ሩቅ አስቦ – ሩቅ ለመጓዝ የተነሳው ብልጽግና!

ኢትዮጵያ በሥነ ፈለክ ምርምር መስክ ተጠቃሽ አገር ነች፡፡ ይህን የአገራችንን ሁኔታ የተገነዘበው የዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚ ህብረት፤ በ2011 ዓ.ም በአንድሮሜዳ ህብረ ኮከብ ውስጥ የሚገኙትን አንድ ኮከብና አንድ ኤክሶ  ፕላኔት ኢትዮጵያ እንድትሰይም ዕድል ሰጥቶ ነበር፡፡ ስለዚህ አገራችን በህዋ ሳይንስ ዘርፍ ያላት ተሳትፎ አሁን በሚገኝበት ደረጃ መሆኑ የሚያስቆጨን ቢሆንም፤ ለቴክኖሎጂው ዘርፍ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ፓርቲያችን ከተመሠረተ ወዲህ አገራችን […]