የአደረጃጀት ዘርፍ የ2014 የስራ አፈጻጸም ማጠቃለያና የ2015 መነሻ እቅድ ኦሪየንቴሽ ሀገራዊ የውይይት መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

#DIREPROSPERITY🇪🇹 ሀምሌ 25/2014

የአደረጃጀት ዘርፍ የ2014 የስራ አፈጻጸም ማጠቃለያና የ2015 መነሻ እቅድ ኦሪየንቴሽ ሀገራዊ የውይይት መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚቆየው የአደረጃጀት ዘርፍ የ2014 የስራ አፈጻጸም ማጠቃለያና የ2015 መነሻ እቅድ ኦሪየንቴሽ ለመስጠት የተዘጋጀ ሀገራዊ የውይይት መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ አንድ ሀገራዊ አሰተሳሰብ እና ራዕይ በመሰነቅ እና ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ለዚህም በቁርጠኝነት በመታገል የመላው የአስተዳደራችንን ነዋሪዎች ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቀሚነት ማረጋገጥ የሚያስችል አደረጃጀቶችንና የአመራር ስምሪት እንዲኖር በማድረግ በአስተዳደራችን የለውጥ አመራሮች ውጤታማ ስራ የተፈጠረውን ህዝባዊ አንድነትና መነቃቃት ተጠቅመን በቁርጠኝነት ሌት ተቀን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

የብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ካሊድ አልዋን ፓርቲያችን በአሁኑ ሰኣት በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ 12 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያንን በማቀፍ በአባላት ቁጥሩ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም እና ከአለም ደግሞ ከቀደምት 10 ፓርቲዎች ተርታ የሚሰለፍ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ ሲሆን ከነዚህ መካከል የ63,521 አመራሮች እና የ11,146,934 አባለት በድምሩ የ11,210,455 አመራሮች እና አባላት ሙሉ መረጃ በዘመናዊ የዲጂታል የመረጃ ቋት(ዳታ ቤዝ) ውስጥ ተመዘግበውና ተደራጅቶ አንደሚገኝ ገልጸዋል።

የጉባኤው የክብር እንግዳና የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሃር በድሬዳዋ ብቁ እና የተናበበ የፓርቲ መዋቅር እንዲኖር በማስቻል ሁሉም አደረጃጀታችን ጠንካራ እና ተልዕኮውን በአግባቡ የሚወጣ በማድረግ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ያስቀመጥነውን ግብ ሊያሳካ የሚያስችል መዋቅር የፈጠርንበት በጀት አመት ነበር፡፡

ይህንንም የአስተዳደራችን የ2014 በጀት ዓመት ሪፖርት ውስጥ ድሬዳዋ አስተዳደር በጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ለወደብ ቅርበት ያላትና በተዘረጋላት ዘመናዊ የመሰረተ ልማት አውታሮች የአየርና የየብስ ትራንስፖርት ያላት እንዲሁም በኢንዱስትሪ፣ በንግድ እና በአገልግሎት ዘርፍ እምቅ ኢኮኖሚያዊ አቅም ያላት ሲሆን ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር የሚችል የኢንዱስትሪ ፓርክ፣በርካታ ዘመናዊ ፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎች፣ አዲሱ የባቡር መስመር አገልግሎት፣የገቢ ንግድን ለማሳለጥ በግዙፍነቱ ግንባር ቀደም የሆነ የደረቅ ወደብ ተገንብቶ የተጠናቀቀበት፣ በተጨማሪም በሀገራችን አዲስና ለመጀመሪያ ጊዜ በአስተዳደራችን ተግባራዊ የሚደረገው ነፃ የንግድ ቀጠና ተፈፃሚ ሲሆን አስተዳደራችንን በንግድ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት መስፋፋትና ዕድገት በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረን ተፅዕኖ ፈጣሪነት የሚያጎላና የብልፅግና ጉዞአችንን የሚያፋጥን ይሆናል ብለዋል፡፡

በመርሃግብሩ መሰረት ክልሎችና አዲስ አበባ አስተዳደር የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ዓመታዊ ሪፖርት በቅርንጫፍ ዘርፍ ሀላፊዎች እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በነገው እለት በቀረቡት ሪፖርቶች ውይይትና የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ የ2015 በጀት ዓመት መነሻ እቅድ ጨምሮ የቀሩት በመርሃግብሩ የተያዙ ጉዳዮች የሚቀርብ ይሆናል።

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *