በድሬዳዋ የብልፅግና ፓርቲ የመሠረታዊ ድረጅቶች የ2014 በጀት ዓመት ኮንፍረንስ አካሄዱ።

#DIREPROSPERITY🇪🇹 ነሀሴ 14/2014

በድሬዳዋ የብልፅግና ፓርቲ የመሠረታዊ ድረጅቶች የ2014 በጀት ዓመት ኮንፍረንስ አካሄዱ።

በድሬዳዋ የብልፅግና ፓርቲ የመሠረታዊ ድረጅቶች የ2014 በጀት ዓመት በሴክተሮች፣ በከተማ ቀበሌና በገጠር ክላስተሮች ከአባሎቻቸው ጋር ኮንፍረንስ አካሄዱ።

በተካሄደው ኮንፈረንስ መሰረታዊ ድርጅቶች የ2014 የፓርቲ ስራዎችን መነሻ በማድረግ የ2014 አ.ም ግማሽ አመት ሪፖርት፣ የኢንስፔክሽን ሪፖርትና የ2015 እቅድ ቀርቦ ውይይት በማድረግ ያጸደቁ ሲሆን በአመቱ ማጠቃለያ የተካሄደው የአባለት ግምገማ ውጤት ቀርቦ በማጸደቅና የተመለመሉ እጩ አባላትን ወደ ሙሉ አባል እንዲሆኑ ተደርጓል።

በመጨረሻም የመሰረታዊ ድርጅት አመራሮችና የኢንስፔክሽን አባላት ምርጫ ተካሂዶ ማሟያ የሚያስፈልጋቸው መዋቅሮች እንዲሟሉ በማድረግ ኮንፈረንሶቹ በድምቀት ተጠናቀዋል።

በነገው እለት በከተማ አቀፍ ደረጃ የብልጽግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የ2014 በጀት አመት የማጠቃለያ ኮንፈረንስ በማዕከል ይካሄዳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *