በድሬዳዋ የ4ኛ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መዝጊያ መርሃግብር በአንድ ጀንበር 700 ሺህ ችግኝ ተተከለ።

#DIREPROSPERITY🇪🇹 ነሀሴ 8/2014

በድሬዳዋ የ4ኛ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መዝጊያ መርሃግብር በአንድ ጀንበር 700 ሺህ ችግኝ ተተከለ።

የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ መትከል ስነ-ስረአት በተመረጡ በተለያዩ የከተማና የገጠር ቀበሌዎች ቦታዎች ተካሂዷል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት፣ የድሬዳዋ አስተደደር የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ የተከበሩ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ አስተዳደር ተወካዮች የተከበሩ አቶ አብዱልጀዋድ መሀመድ እና የተከበሩ ዶ/ር ቢፍቱ መሀመድ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በአገር አቀፍ ደረጃ ‘’አረንጓዴ አሻራችን ለትውልዳችን‘’ በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ ያለው መርሀግብር አካል የሆነ የችግኝ ተከላ ስነ-ስርአት በዛሬው እለት ዲፖ በሚገኘው የሲቪክ ማእከል ግቢ ውስጥ ተካሂዷል ፡፡

በችግኝ ተከላ መርሀግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን በመጀመሪያ የአንድነታችን አርማ እና የብልጽግናችን ማብሰሪያ ለሆነው የህዳሴ ግድብ 3ኛ ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቅ የእንኳን ደስ ያላቹ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ ከአሁን በፊት ድሬዳዋ ሲያጋጥማት የቆየውን የድርቅና የጎርፍ አደጋ ለማስቀረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖለው ገልጸዋል፡፡ በመሪ ቃሉ መሰረትም የበረሃዋ ንግስት የሆነች ድሬዳዋን ሳይሆን የለመለመች ድሬዳዋን ለትውልድ ለማስረከብ ሁሉም የአስተዳደሩ አመራርና ነዋሪ ችግኞችን በመትከል ብቻ ሳይሆን የተተከሉትንም ተንከባክቦ በማሳደግ የዜግነት ግዴታውን መወጣጥ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

በዛሬው እለት የሲቪክ ሴንተርን ጨምሮ በ8 የከተማና የገጠር ቀበሌዎች መርሃግብሩ ተካሂዷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *