በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጲያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል ወረዳ 2 ወጣቶች ማስተባበሪያ ከድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ ስራዎች መክፈቻ አካሄደ

በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጲያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል ወረዳ 2 ወጣቶች ማስተባበሪያ ከድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ ስራዎች መክፈቻ አካሄደ፡፡

በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ደረጀ ፀጋዬ እንደተናገሩት በዘንድሮ የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በ14 የትኩረት መስኮች ላይ ከተጀመሩ የልማት ስራዎች መሀል የመንገድ ደህንነት ስራ አንዱ መሆኑን አስታውሰው ይህ እንዲሳካ የወጣት አደረጃጀቶች ሚና የጎላ ነው ብለዋል። በተለይም በክረምት በጎ ፍቃድ ላይ ወጣቱን በግንባር ቀደምትነት በማሳተፍ እንደ መንግስት የሰራናቸው ስራዎች ውጤታማ ነበሩ ነው ያሉት።

በዘንድሮውም በወረዳ 2 የሚገኙ ወጣቶችም በክረምት በጎፍቃድ ማህበረሰባቸውን ለማገልገል ያሳዩት ቁርጠኝነት በሌሎች ወረዳዎችም እንዲደገም ጥሪ አቅርበዋል።

የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሹክሪ አብዱረህማን በበኩላቸው አሁን ላይ ለበርካቶች ህልፈት ምክንያት የሆነውን የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ ጠቁመው በተለይ ወጣቱ ማህበረሰቡን በማንቃት እና በትራፊክ አደጋ አስከፊነት ላይ ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ ለምንሰራው ስራ አብሮን ሊንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ ማብቂያም በበጋው የበጎ-ፍቃድ ስራውች ከፍተኛ አስተዋፆ ላበረከቱ ወጣቶች የምስጋናና የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *