“ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሀሳብ በ10 የስልጠና ማዕከላት ለ12 ቀናት ሲሰጥ የቆየው 2ኛ ዙር የከፍተኛ እና የመካከለኛ አመራሮች የስልጠና መድረክ በሁሉም ማዕከላት በዛሬው እለት ተጠናቋል።

ጥቅምት 11 ቀን 2016

#DIREPROSPERITY🇪🇹

“ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሀሳብ በ10 የስልጠና ማዕከላት ለ12 ቀናት ሲሰጥ የቆየው 2ኛ ዙር የከፍተኛ እና የመካከለኛ አመራሮች የስልጠና መድረክ በሁሉም ማዕከላት በዛሬው እለት ተጠናቋል።

የስልጠና መርሀ ግብሩ ፓርቲያችን በምርጫ ማግስት ለህዝብ ቃል የገባቸውን ጉዳዮች በተሳካ ሁኔታ ለመፈፀም አቅም የሚያዳብርበት፣ አመራሩ ውስጣዊ አንድነቱን አጠናክሮ ለቀጣይ ሀገራዊ ተልእኮ በታላቅ ተነሳሽነት ወደፊት እንዲጓዝ የሚያስችል ነው።

በሁሉም ማዕከላት የነበሩ መርሀ ግብሮች በከፍተኛ ክትትል እና የምዘና ስርአት የተካሄዱ ሲሆን የፓርቲያችን ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ በአካል በመገኘት ጭምር የስራ መመሪያዎችን ለተሳታፊዎች ሰጥተዋል።

ሰልጣኞች በአስሩም ማዕከላት የነበሩ ስልጠናዎች በሰነድ እና በአሰልጣኞች ካገኙት እውቀት በተጨማሪ እንደ ሀገር ያስመዘገብናቸውን በየክልሉ የተገኙ ድሎች በመስክ ምልከታ እንዲገነዘቡ በርካታ እድሎችም ተመቻችተው ነበር።

በተጨማሪም በፓርቲ መሰረታዊ እሳቤዎች በመመራት ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ነባራዊ ዐውዶችን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የአመራር ሚናውን ለመወጣት እራሱን ያዘጋጀበት የስልጠና ጊዜ ሲሆን በዛሬው እለት በሁሉም ማዕከላት በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል።

#prosperity

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *