የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ 1ኛ ቅድመ ጉባዔ ኮንፈረንስ መካሄድ ሊጀመር ነው፡፡
ኮንፈረንሱ በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ ቀበሌ እና ወረዳዎች ደረጃ ከነሃሴ 11 – 20/2014 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
በኮንፈረንሱ የብልፅግና ወጣቶች ሊግ የጉባዔ ሪፓርት፣ ፕሮግራም እና የሊጉ ህገ ደንብ ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን ከ3.5 ሚሊዮን በላይ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አባላት እንደሚሳተፉ የሊጉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አክሊሉ ታደሰ ገልፀዋል፡፡
በኮንፈረንሶቹም በመጭው መስከረም ወር መጨረሻ ለሚካሄደው የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ 1ኛ ጉባኤ ተሳታፊዎች የሚመረጡበት ይሆናል።