የአረንጓዴ አሻራ መዝጊያ መርሃግብር ታሳቢ ያደረገ የ36ኛው ሣምንት ከተማ አቀፍ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።

#DIREPROSPERITY🇪🇹 ነሀሴ 7/2014

የአረንጓዴ አሻራ መዝጊያ መርሃግብር ታሳቢ ያደረገ የ36ኛው ሣምንት ከተማ አቀፍ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።

ድሬደዋን ለነዋሪዎች ምቹና የቱሪዝም መስህብ ለማድረግ ለ36ኛ ዙር ከተማ አቀፍ የጽዳት ዘመቻ የአረንጓዴ አሻራ መዝጊያ መርሃግብር ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በምስጋና ንግግራቸው ገልጸዋል።

አክለውም የተጀመሩ የፅዳት ዘመቻዎችና የአረንጓዴ አሻራ የማልበስና የመንከባከብ ተግባራት በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና በነገው እለት በአስተዳደሩ በተመረጡ ቦታዎች በሚካሄደው በአንድ ጀንበር 700ሺህ ችግኝ ተከላ መርሃግብር የአስተዳደሩ ነዋሪዎች በስፋትና በባለቤትነት እንዲሳተፉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ከማለዳ 12 ሰአት መነሻው ከሳቢያን ቻይና ድልድይ /የችግኝ ጣቢያ/ ሆኖ እስከ መልካ ድልድይ ድረስ የዋና መንገዱን ግራና ቀኝ ፅዳት ሥራ ጀምሮ በተካሄደው ዘመቻ የአስተዳደሩ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም የድሬደዋ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ተገኝተዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *