የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍና ክትትል አስተባባሪ ሰብሳቢ የሚመራ ልኡካን ቡድን በብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤትና በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲን ጉብኝት አደረጉ፡፡

#DIREPROSPERITY🇪🇹 ነሀሴ 11/2014

የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍና ክትትል አስተባባሪ ሰብሳቢ የሚመራ ልኡካን ቡድን በብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤትና በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲን ጉብኝት አደረጉ፡፡

7 ልኡካን ቡድንን የያዘው የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የምሁራን ልኡካን ቡድን በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት የዩኒቨርሲቲውን የስራ እንቅስቃሴ የጎበኙ ሲሆን ልዑካን ቡድኑ ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሂደቱን በዘመኑ ቴክኖሎጂ በተደገፈ ሁኔታ ለተማሪው ለማድረስ እያደረገ ያለው ጥረትና የማኅበራዊ አገልግሎት ከመስጠት አኳያም ወደ ማኅበረሰቡ ለመድረስ ያቋቋመው ዘመናዊ የማኅበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ እጅግ የሚበረታታታና ጠቃሚ ልምድ የወሰዱበት መሆኑን የልኡካን ቡድኑ መሪና የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የድጋፍና ክትትል አስተባባሪ ሰብሳቢ አቶ አስቻለው መሸሻ ተናግረዋል።

አሳተባባሪው አክለውም የሁለቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የእርስ በእርስ ግንኙነት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀው በቀጣይም የተቋማቱን የእርስ በእርስ ግንኙንት የሚያጠናክሩ ስራዎች በጋራ የሚሰሩ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የድጋፍና ክትትል አስተባባሪ ሰብሳቢ አቶ ኬኪያ ዲሪባ በበኩላቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካካል የሚደረጉት የእርስ በእርስ ግንኙነቶች ለየተቋማቱ እድገትና ለውጥ የሚኖራቸው ፋይዳ እጅግ የጎላ በመሆኑ የዚህ አይነቱ የልምድ ልውውጥን አጠናክሮ በመቀጠል ለጋራ እድገት ተባብሮ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *