“እኔ ሰላም ስሆን ሀገር ሰላም ትሆናለች”

ሁለንተናዊ ብልፅግና የተረጋገጣባት ሀገር ለመፍጠር ሰላም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ ያለ ሰላም ብልፅግና ሊረጋገጥ፤ የሀገር እቅዶች እና ግቦች ፈፅሞ ሊሳኩ አይችሉም፡፡

ብልፅግና ፓርቲም ይህን ጉዳይ ጠንቅቆ በመረዳት፤ ለሀገር የብልፅግና መሰረት የሆነውን የሰላም ሁኔታ የሚታዩበትን እክሎች እልባት ለመስጠት፤ በጠንካራ ፖሊሲዎች የዳበር ስትራቴጂ በመቀየስ፤ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

ሰላም የሚገኘው በግለሰብ ደረጃ ከሚመነጭ አስተሳሰብ ነውና ለኢትዮጵያ ሰላም መረጋገጥ እኔም፣ አንተም፣ አንቺም ከፍተኛ ሀላፊነት አለብን፡፡ “እኔ ሰላም ስሆን ሀገር ሰላም ትሆናለች” ከሚል ውጤት ካለው የብዜት አስተሳሰብ ሁላችንም ብንነሳ፤ ኢትዮጵያን ሰላም ማድረግ እጅግ ቀላል እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ምክንያቱም የብዙሀን ድምር እሳቤ የሚሆነው የግለሰብ የአስተሳሰብ ውጤት ነውና፡፡

በመሆኑም ይህን ሀቅ በመረዳት እንደ ፓርቲ የቀየስናቸው የሰላም ስትራቴጂዎች በሙሉ፤ ከግለሰብ እስከ ማህበረሰብ ያለውን የስነ-አእምሯዊ መስተጋብር የሚዳስሱ በመሆናቸው፤ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና መረጋገጥ መሰረት ለሆነው የሰላም ሂደት ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለህዝቦቿ!!

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *