#DIREPROSPERITY
ሀምሌ 27/2014
የአደረጃጀት ዘርፍ የ2014 የስራ አፈጻጸም ማጠቃለያና የ2015 መነሻ እቅድ ኦሪየንቴሽ ሀገራዊ የውይይት መድረክ ተጠናቀቀ።
ለሶስት ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ ሲካሄድ የቆየው የብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ የ2014 የስራ አፈጻጸም ማጠቃለያና የ2015 መነሻ እቅድ ኦሪየንቴሽ ሀገራዊ የውይይት መድረክ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሀር፣ የዋናው ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ም/ ኃላፊ አቶ ካሊድ አልዋን፣ የፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ፣ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና የጉባኤው ተሳታፊዎች በተገኙበት የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የችግኝ ተከላና የመስክ ምልከታ በማድረግ ተጠናቀቀ።
በነበረው ቆይታ በልማት በድሬዳዋ ከፍተኛ መነቃቃት የታየበትና በአደረጃጀት ዘርፍ ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆኑ ሞዴል ስራዎች በልምድ የተቀሰመበት መሆኑ ተገልጿል።
የፓርቲው አደረጃጀት መሰረቱ የጠነከረና ህይወት ያለውና ውጤታማ መዋቅር እንዲሆን በማንሳት በ2015 በእቅድ የማይመራና ያልተደራጀ ሊኖር እንደማይገባ የብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የዋናው ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ም/ ኃላፊ አቶ ካሊድ አልዋን አሳስበዋል።
በመጨረሻ በአሰተዳደሩ የፓርቲ ጽ/ቤት እና የቀበሌ 03 ጉብኝት እንዲሁም የነባሩ ባቡር ሽርሽርና አጠቃላይ መስተንግዶ መደሰታቸውን የጉባኤው ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
![]()
