#DIREPROSPERITY ነሀሴ 9/2014
2ኛ ዙር በህዝብ ውክልና አወጣጥ ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ ተወካዮች በ1ኛው ዙር የህዝብ ውክልና አወጣጥ መድረክ ላይ ከህዝብ በተሰጡ አስተያየቶች መሰረት በተሰሩ የ5ተቋማት ሪፖርት ላይ የውይይት መድረክ በምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን መሪነት በምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡
በውይይት መድረኩ ከነዋሪው ጋር በተደረገው የ1ኛውን ዙር የህዝብ ውክልና አወጣጥ መድረክ ከህዝቡ የተነሱ አስተያየቶች መሰረት የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት ያቀረቡት ተቋማት ጤና ቢሮ ፣ ትምህርት ቢሮ እና የግብርና ውሀ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮዎች ከተማ ስራ አስኪያጅና የማብራት ሀይል አገልግሎት ሲሆኑ ሪፖርታቸውንም በተቋማቸው ሃላፊዎች በዝርዝር አቅርበው በምክር ቤቱ አባላት ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በመቀጠልም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ ተወካዮች የተከበሩ ዶ/ር ቢፍቱ መሀመድ እና የተከበሩ አቶ አብዱልጀዋድ መሀመድ እንደገለጹት በአስተዳደሩ ነዋሪዎች የተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን በአንዴ መልስ መስጠት እንደማይቻል ነገር ግን የህዝቡን ዋና ዋና ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት በየደረጃው የሚፈቱ ችግሮችን በመለየት ችግሮቹ እስኪፈቱ ድረስ የጋራ ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም በቀጣይ ስለሚካሄደው 2ኛ ዙር የህዝብ ውክልና አወጣጥ ላይ በመንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ የተከበሩ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ አቅጣጫ እንዲሁም በምክር ቤቱ ጸሀፊ የተከበሩ አቶ ስንታየሁ ማሞ ማብራሪያ ተሰጥቶበት የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡
በተያያዘ ዜናም በከተማና በገጠር ቀበሌዎች ከህዝብ ጋር የሚካሄደው 2ኛው ዙር የህዝብ ውክልና አወጣጥ የውይይት መድረክ ከእሮብ ነሀሴ 11/2014 እስከ ነሀሴ 25/2014 ድረስ እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል፡፡