ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያን እንገነባለን! እኛ ብልጽግና ነን!

ኢትዮጵያ የብሔር፣ የባህል፣ የሐይማኖት፣ የፖለቲካ አመለካከት ወዘተ ብዝሃነት ያላት፤ በዚህም መነሻ፤ የተለያዩ ጥቅሞችና ፍላጎቶች የሚንጸባረቁባት አገር ናት፡፡ ስለሆነም የምትገነባው ኢትዮጵያ የእምነት፣ የብሔር እና የፖለቲካ አመለካከት ወይም የጥቅም እና የፍላጎት ብዝሃነት የምታንፀባርቅ መሆን ይኖርባታል፡፡ ይህን በአግባቡ የተረዳውና ለጉዳዩም ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ ትግል የጀመረው ፓርቲያችን ብልጽግና ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያን የመገንባትን አስፈላጊነትን በፖለቲካ ፕሮግራሙ ከመግለጽ ባሻገር፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት ይህን ዓላማ ለማሳካት የሚያስችሉ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡

ብልጽግና እንደ አገር ቀስፈው ከያዙን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች ለመውጣትና በተከታታይ አገር የመምራት ኃላፊነትን የጨበጡ የአገራችን መንግስታት ሊሻገሩት ያልቻሉትን ቅቡልነት የማጣት ችግር ተሻገሮ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ዘላቂ አገረ መንግስት ለመገንባት ‹‹ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያ›› መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቶ ያምናል፡፡  

በዚህ መነሻነት፤ ፓርቲያችን ብልጽግና የፖለቲካ ፕሮግራሙ ዓላማ አድርጎ ከያዛቸው ጉዳዮች አንዱ፤ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው አገረ  መንግስት መገንባትን ሲሆን፤ ይህ ከግብ ሊደርስ የሚችለው፤ ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያ በመፍጠር ብቻ ነው፡፡

የፓርቲያችን ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በመጀመሪያው የፓርላማ ንግግራቸው እንዳሉት፤ ሁሉም የአገራችን ዜጎች ‹‹ሲኖሩ ኢትዮጵያዊ፤ ሲሞቱ ኢትዮጵያ›› መሆን የሚችሉበትን ሁኔታ በተሟላ መልኩ መፍጠር የሚቻለው፤ “ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያ” በመገንባት ነው፡፡  

ኢትዮጵያውያን ደማቸውን አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው በመስዋዕትነት ነጻነቷን ጠብቀው ከእኛ ያደረሷት ኢትዮጵያ፤  የበለጸገች ብቻ ሳትሆን በአምሳላቸውም የተቀረፀች ኢትዮጵያ መሆን ይኖርበታል፡፡ እንዲህ ዓይነት ኢትዮጵያንም  በወዛቸው እንደትበለፅግ፤ በደማቸው ታፍራ፣ ተከብራ፤ አንድነቷ ተጠብቆ ለዘላለም ፀንታ እንድትኖር ለማድረግ ይተጋሉ፡፡

አገራችን በመደመር ጎዳና ወደ ብልጽግና እንድታመራ፤ አንዱ በይ ሌላው የበይ ተመልካች የሚሆንበትን ሁኔታ ከመሠረቱ መቀየር ይኖርበታል፡፡ ይህን የተረዳው ፓርቲያችን ብልጽግናም ባለፉት ሦስት ዓመታት የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ችግሩን ለመፍታት ተንቀሳቅሷል፡፡ ለፓርቲያችን ብልጽግና፤ የሀገረ መንግስትና የብሔረ መንግስት ግንባታ ትግል ዋና ማጠንጠኛም ጠንካራ ኢትዮጵያን የመገንባት ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የሚገኝ ስኬትም ምላሽ የሚፈልግ አገራዊ አጀንዳ ሆኖ የቆየውንና ከቅቡልነት ችግር የተላቀቀ አገረ መንግስት ለመገንባት ያስችለናል፡፡  

የመንግስት ቅቡልነት አጅንዳ የከረመ አጀንዳ ቢሆንም፤ ከቅርብ ዓመታት (በተለይም ከ2007) ወዲህ በአገራችን የታዩ የተለያዩ ችግሮች በግልጽ የሚያመለክቱን፤ ኢትዮጵያ  ወደ መሠረታዊ የአገረ መንግስት ግንባታ ሥራዎች መመለስ ያለባት መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ የአገረ መንግስት እና የብሔረ መንግስት ግንባታ ትግላችን መነሻ ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያን የመፍጠር ጉዳይ ነው፡፡  

በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር አንዱ ባለ ጉዳይ ሌላው የዳር ተመልካች የሚሆንበትን ሁኔታ በማስወገድ፤ ብሔራዊ መግባባትን ፈጥረን መጓዝ ካልቻልን፤ የሰላም፣ የልማት እና የዴሞክራሲ ጉዟችን ይደነቃቀፋል ብቻ ሳይሆን፤ አገራዊ ህልውናችንንም ጠብቀን መዝለቅ አንችልም፡፡

ይህን ሁኔታ በአግባቡ የተረዳውና የብልጽግና እርሾ የሆነው የለውጥ ኃይል፤ የተዛነፉ ነገሮች እንዲስተካከሉና ሁሉም ዜጎች በእኩልነት ተሳትፎ በማድረግ መወሰን የሚችሉበት አካታች የፖለቲካ መድረክ እንዲፈጠር ለማድረግ ታግሎ ብልጽግናን እውን አድርጓል፡፡ አባል እና አጋር የሚል የፓርቲ አደረጃጀት እንዲቀር በማድረግም ሁሉም ፓርቲዎች የሚሳተፉበት እና እኩል የመወሰን የሚያገኙበት ብልጽግና የተሰኘ አገራዊ ፓርቲ መስርቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ክልሎች በምስለኔ እና በሞግዚት የሚተዳደሩበት አሰራር ተወግዶ፤ የተሟላ ራስን በራስ የማስተዳደር ዕድል የሚያገኙበት፤ በዚህም እውነተኛ የፌዴራል ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ የሚቻልበት አዲስ ምዕራፍ እንዲከፈት አደርጓል፡፡ የሁሉንም ዜጎች ተሳትፎ በማረጋገጥ፤ ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያን የመገንባት ቁርጠኝነቱንም አሳይቷል፡፡  

የዚህ ቁርጠኝነቱ ሌላ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባው፤ ፓርቲያችን ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ ሌሎች አራት የአገራችን ቋንቋዎች የፓርቲውየሥራ ቋንቋ ሆነው እንዲያገለግሉ ውሳኔ ማድረጉ ነው፡፡ ይህም ፓርቲያችን ብልጽግና ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለውን ጠንካራ እምነት አመላካች ሲሆን፤ በሰላም ሚኒስቴር አማካይነት እየተከናወኑ ካሉ በጥናት የተደገፉ ሰፋፊ የብሔራዊ መግባባት ሥራዎች ጋር ተዳምሮ፤ አገራዊ አንድነታችንን ይበልጥ በማጠናከር፤ እየተንከባለለ ከኛ የደረሰውን የመንግስት የቅቡልነት ችግር በማስወገድ፤ ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያን በመፍጠር ወደ ብልጽግና የሚደረገው ጉዞ የተሳካ እንዲሆን ምቹ መደላድልን ይፈጥርልናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፤ በግንቦት ወር መጨረሻ የሚካሄደው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያን የመገንባት ግባችን አንድ ምሰሶ አድርገን የምንመለከተው ነው፡፡ እንደሚታወቀው፤ ኢትዮጵያ የተለያዩ እምነቶች፣ ብሔሮች፣ ቋንቋዎች እና ባህሎች አገር ብቻ ሳትሆን፤ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች፣ ጥቅሞች እና ፍለጎቶች የሚንፀባርቁባት አገር ነች፡፡ በመሆኑም፤ በሁሉም ደረጃ ያሉ ምክር ቤቶች በአንድ ፓርቲ ተመራጮች የሚያዙበት ሁኔታ፤ የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ በፍፁም የማያንፀባርቅና ባለፉት ሰባት ዓመታት ለተመለከትናቸው፤ አገራዊ ደህንነትን ለአደጋ የሚያጋልጡ ችግሮች ጭምር መንስዔ ተደርጎ ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ነው ብሎ ያምናል፡፡

ስለዚህ በየደረጃው የሚገኙት ምክር ቤቶች የኢትዮጵያን ህዝቦች ትክክለኛ ፍላጎትን የሚያንፀባርቁ ምክር ቤቶች እንዲሆኑ ማድረግ ‹‹ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያን›› የመፍጠር የፖለቲካ ግባችን አንድ አካል ነው፡፡ በመሆኑም ፓርቲያችን ብልጽግና በዘመናዊ የአገራችን የፖለቲካ ታሪክ የመጀመሪያውን ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ተአማኒነት ያለውና ዴሞክራሲያዊ የሆነ ምርጫ ለማካሄድ ያሳየው በተግባር የተገለፀ ቁርጠኝነት፤ ዜጎች የሚፈልጉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የሚችሉበትን ሁኔታ በማመቻቸት፤ በአገራችን የሚታዩ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች በየደረጃው ባሉ የህዝብ ምክር ቤቶች ውክልና ለማግኘት የሚችሉበትን ዕድል ክፍት በማድረግ፤ ምክር ቤቶቹ የኢትዮጵያን ህዝብ ትክክለኛ ፍለጎት የሚያንፀባርቁና ‹‹ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያን›› የመፍጠር ከልብ የመነጨ ፍላጎታችንን የሚያረጋግጥ ነው፡፡

የመንግስት የቅቡልነት ችግር የሚፈታው በምርጫ ብቻ ባይሆንም፤ በአሁኑ ጊዜ በዋናነት ቅቡልነት የሚመነጨው ከምርጫ በመሆኑ፤ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ተአማኒነት ያለውና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን፤ የመንግስትን የቅቡልነት ችግር በማስወገድና የህዝቡን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ምክር ቤቶች እንዲቋቋሙ በማድረግ ‹‹ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያን›› የመፍጠር ግባችንን ለማሳካት ያስችለናል ብለን እናምናለን፡፡ ይህም አገራዊ አንድነቱን ይበልጥ ለማጠናከርና ወደ ብልጽግና የሚደረገውን ጉዞ ለማሳካት ምቹ መደላድል ይፈጥርልናል፡፡  

የፓርቲያችን ሊቀመንበር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በ2011 ዓ.ም በስዊትዘርላንድ በተካሄደው የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ ‹‹በፍጥነት ለመጓዝ ከፈለግህ ብቻህን ሩጥ፤ ረጅም መንገድ ለመጓዝ ከቆረጥክ ከሌሎች ጋር አብረህ ተጓዝ›› እንዳሉት፤ አገራችን ፍጥነት የታከለበት ረጅም ርቀት መጓዝ እንድትችል፤ ፓርቲያችን ብልጽግና ‹‹ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያን›› ለመገንባት የጀመረውን ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

ዕጣ – ፊንታችን አንድም ብዙም ሆኖ የተሳሰረ በመሆኑ፤ ፍጥነት የታከለበት ረጅም ርቀት ለመጓዝና እንደ አገር ቀስፈው ከያዙን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች በፍጥነት ለመወጣት፤ በመደመር ጎዳና በህብረት፣ በጋራ፣ በመተሳሰብ ወደ ብልጽግና ለመግባት ‹‹ኢትዮጵያውያንን የምትመስል ኢትዮጵያን›› እንገነባለን፡፡   

Loading

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *