ብልጽግና የዛሬና የነገ ፓርቲ!
ወርቅ ከማዕድናት በተለየ በሁሉም ዘንድ የመወደድና የመመረጥ ክብር የተጎናጸፈው፤ ከአፈር መገኘቱ ተዘንግቶ አይደለም። በብርቱ እሳት ተፈትኖ በማለፉ እንጂ፡፡ ብልጽግናም በፈተና ውስጥ ተወልዶ በፈተና ውስጥ እያለፈ የመጣ፣ ወደፊትም ፈተናዎችን በጥበብ እያለፈ የሚቀጥል ከዘመን ጋር ራሱን እያደሰና እየለወጠ የሚሄድ ፓርቲ ነው። ብልጽግና የዛሬና የነገ ፓርቲ በመሆኑና ብሩህ ተስፋን ሰንቆ ለኢትዮጵያ ልዕልና በመትጋቱ ብዙዎች ተስፋቸውን ጥለውበታል፣ ብዙዎችም በፍቅር